
ባህር ዳር፤ግንቦት 8/2017 (ኢዜአ)፦የባህርዳር ከተማን ሰላም ለመጠበቅና የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ የከተማዋ ነጋዴዎች ተናገሩ።
"የጥፋት እጆቹና መዘዞቹ " በሚል መሪ ሃሳብ ከባህር ዳር ከተማ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ጋር ዛሬ የውይይት መድረክ ተካሄዷል።
የውይይቱ ተሳታፊ ነጋዴ ወይዘሮ ዘነበች መንግስቴ፤ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።
ይህም በሸማቹ ህብረተሰብ ላይ ችግር እየፈጠረ እንደሚገኝ ጠቁመው፥ መፍትሄ ለመሻት እየተደረገ ባለው ጥረት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡም ተናግረዋል።
ሌላኛዋ የሸቀጣ ሸቀጥ ነጋዴ ወጣት ምሳነሽ እናናው፤ የጽንፈኝነት አስተሳሰብን መከላከል የንግዱ ማህበረሰብን ጨምሮ የሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነት መሆን እንዳለበት ገልጻለች።
በዚህም የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ራስን መፈተሽና ከጽንፈኝነት አስተሳሰብ ከማውጣት በዘለለ በተሳሳተ መንገድ ውስጥ ያሉ ወገኖችን መምከር ይጠበቅበታል ብለዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህር ዳር ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ብርሃን ንጉሴ በሰጡት ማብራሪያ፥ የጽንፈኝነት አስተሳሰብ የወለደው የሰላም እጦት በክልሉ ተጽእኖ አሳድሯል።
ይህም የንግዱ ማህበረሰብ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ ስራውን እንደልቡ እንዳይሰራና ተረጋግቶ እንዳይኖር በማድረጉ በሸማቹ ላይም ተጽእኖው እንዲኖር አድርጓል ብለዋል።
የንግዱ ማህበረሰብም መንግስት ችግሩን በውይይትና በንግግር ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት ማገዝና መደገፍ ይጠበቅበታል ብለዋል።
በተጨማሪም የንግዱ ማህበረሰብ ጽንፈኞችን በማጋለጥ ለህግ የበላይነት መረጋገጥ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚጠበቅበትም አሳስበዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026