
ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 8/2017 (ኢዜአ) ፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ9 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ አጸደ አይዛ እንደገለጹት፤ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የተሰጠው ለ151 ባለሀብቶች ነው።
ባለሃበቶቹ ፈቃዱ የተሰጣቸው በግብርና፣አገልግሎትና ኢንዱስትሪ ዘርፎች ለመሰማራት ጠይቀው መሆኑን ጠቅሰው፤ ከ33 ሺህ ለሚልቁ ሰዎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩ የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ላይ 90 ሺህ 575 ሄክታር መሬት ተለይቶ መቀመጡን ጠቅሰው፤ እየመጡ ያሉ በርካታ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ጥያቄዎች አዋጪነታቸው እየታየ እንደሚስተናገድ አስረድተዋል።
ከዚህ ሌላ የተሰጣቸውን መሬት ሳያለሙ አጥረው ያስቀምጡና ላልተገባ ስራ ሲጠቀሙ የተገኙ 34 ባለሀብቶች ውላቸው መቋረጡን ጠቁመው፤ ለ62 ደግሞ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።
ክልሉ ሰፊ ጸጋ እንዳለው አመልክተው፤ ክልሉ ከተመሰረተ ወዲህ 350 ባለሀብቶች ፈቃድ ወስደው ስራ ላይ መሆናቸውን አንስተዋል።
የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ፍሬው ሞገስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥በአካባቢው የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እየተነቃቃ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢንቨስትመንት ዘርፉ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ በተቀናጀ መንገድ የመደገፍና ክትትል ስራ እየተከናወነ መሆኑን አመልክተው፤ በገቡት ውል መሰረት ወደስራ ያልገቡትን ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ስራ መጠናከሩን ተናግረዋል።
በከተማው የአንጂዲ ዱቄት ፋብሪካ ባለቤት ወይዘሮ ፀጋነሽ ወልደጊዮርጊስ ፤በመንግስት በኩል የሚደረግ ድጋፍና ክትትል የሚያበረታታ መሆኑን አንስተው፤ አሁን ላይ ድርጅታቸው ከ100 ለሚልቁ ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠሩን ጠቁመዋል።
በቀጣይም ከዚህ በላይ አስፍተው ለመስራት የማስፋፊያ ቦታ ጠይቀው እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የፖስታ እና ማካሮኒ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እየገነቡ ያሉት አቶ እንዳለ ጎአ በበኩላቸው፥ በመንግስት በኩል እየተደረገ ያለው ድጋፍ መልካም መሆኑን ገልጸዋል።
ግንባታው ሲያልቅ ለ200 ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራልም ነው ያሉት።
የክልሉ የስራ ሃላፊዎች በወላይታ ሶዶ ከተማ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ዛሬ ተመልክተዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026