የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ኢምብሬር ኩባንያ በኢትዮጵያ በአቪዬሽን ኢንቨስትመንት የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

May 19, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2017(ኢዜአ)፡- ኤምብሬር የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ በአቪዬሽን ኢንቨስትመንት መሰማራት እንደሚሻ አስታወቀ።

የኩባንያው የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ተቋማዊ ግንኙነት ዋና ስራ አስኪያጅ ሁሴን ዳባስ ኢትዮጵያ የህግ ማዕቀፎችን፣ የኢንቨስትመንት ስነ-ምህዳርና አሰራሮችን በማሻሻል የውጭ ባለሀብቶችን እየሳበች እንደምትገኝ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።

የመንግስት እርምጃ እና አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በመሳብ ከቀዳሚዎቹ ስፍራ እንድትቀመጥ ማድረጉን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያን የአቪዬሽን ዘርፍ ያደነቁ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ግዙፉ እና በዓለም ላይ ከሚገኙ ትላልቅ አየር መንገዶች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል።

በትራንስፖርት ዘርፍ የታየውን እድገትም አስገራሚ ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ሁሉም ዘርፎች ለባለሀብቶች ሳቢ ናቸው ያሉት ስራ አስኪያጁ የትራንስፖርት ዘርፉ በተለይ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ የሚያስችል ሁኔታ አለው ነው ያሉት።

በዚህ ረገድም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የጥገና መስጫዎች፣ የማሰልጠኛ ማዕከላት እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ኤምብሬር ኩባንያ የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንትና የእድገት አካል መሆን እንደሚፈልግ ጠቅሰው በአቪዬሽን ኢንቨስትመንት በተለያዩ ዘርፎች የመሰማራት ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።

ኩባንያው ለመንገደኞችም ሆነ ለጭነት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት አውሮፕላኖችን ያመርታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026