የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የሥራ ስምሪት መርሃ ግብሮችን ከአገራዊ ልማት ጋር በማጣጣም ተግባራዊ ማድረግ ይገባል

May 21, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ ፤ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፦የሥራ ስምሪት መርሃ ግብሮችን ከአገራዊ ልማት ጋር በማጣጣም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።

20ኛው የዓለም ሥራ ድርጅት በሥራ ላይ የተመሰረተ የባለሙያዎች አህጉራዊ ስብሰባ "የማይበገር ማህበረሰብ እና ጤናማ አካባቢ የሰው ኃይልን በብዛት የሚጠቀሙ የኢንቨስትመንት ፕሮግራም አካሄዶች" በሚል መሪ ሀሳብ በአፍሪካ ሕብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።

በስብሰባው የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች፣የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ተገኝተዋል።

የጉባኤው ተሳታፊ የሆኑ 25 የአፍሪካ ሀገራት ምቹ የስራ ምህዳር ለመፍጠር የሚያስችል የጋራ አቋም መግለጫ አውጥተዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የጋራ አቋም መግለጫውን በንባብ ያሰሙ ሲሆን፤የተጠናከረ የሥራ ልማት ቅጥር ፕሮግራም አካሄድ በተገቢው ስትራቴጂ መምራት እንደሚገባ አንስተዋል።

የሥራ ስምሪት መርሃ ግብሮች ከአገራዊ ልማት ጋር በማጣጣም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ በአቋም መግለጫው ተመላክቷል።

የፖሊሲ ወጥነትን ማሳደግ እና በተለያዩ የአፈፃፀም እና የአስተዳደር መዋቅሮች መካከል ያለውን ትብብር ማሻሻል እንደሚያስፈልግም ተገልጿል።

‎የሥራ ገበያን የመተንተን አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ እና የፋይናንስ ተቋማት የኢንቨስትመንት ውሳኔዎችን በመደገፍና በማጠናከር የተፈጠሩ የስራ ስምሪቶችን በተሻለ መንገድ ለመከታተል እንደሚያስችል ተጠቁሟል።

በጋራ አቋም መግለጫ የተቀመጡ ተግባራት አፈፃፀም ሂደትን ለመከታተል ተገቢ የሆነ የክትትል እና የግምገማ ስርዓቶች እና መረጃን መሰብሰብ እና መለዋወጥ እንደሚገባም ተመላክቷል።

የአለም አቀፍ የስራ ድርጅት ሀገራት ይህን የጋራ መግለጫ ገቢራዊ ለማድረግ ለሚጠይቁት ድጋፍ የበኩሉን እንዲወጣ በአቋም መግለጫው ጥሪ ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026