
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር ዘመናዊና ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበች መሆኑን የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 ላይ የተሳተፉ የውጭ ኩባንያዎች ገለጹ።
ከፈጣኑንና ተለዋዋጩ የአለም ነባራዊ ሁኔታ እኩል ለመራመድ የዲጂታል ስነ-ምህዳር መፍጠርና የዲጂታል ክህሎትን ማጎልበት ለነገ የማይባል ሥራ መሆኑ በተደጋጋሚ ይጠቀሳል።
ከፍተኛ የወጣት ቁጥር ባላት ኢትዮጵያም በዲጂታል ቴክኖሎጂ የወጣቱን አምቅ አቅም ተጠቅማ ልማቷን ለማፋጠን የተለያዩ ስራዎች እያከናወነች ትገኛለች።
መንግሥት የቴክኖሎጂ ፈጠራን የሚደግፉ ፖሊሲና ሰትራቴጂዎችን ከመቅረጽ ባለፈ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከላትን እያሰፋ ይገኛል።
ከቀናት በፊት በተካሄደው የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች እየተገበረቻቸው ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ለአለም ለማስተዋወቅ ያስቻለ ነው።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በስታርታፕና በተለያዩ የፈጠራ ውጤቶች ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምርትና አገልግሎትን ማቀላጠፍና ማስፋት መቻሉን ኤክስፖው በተግባር አሳይቷል።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡና በኤክስፖው የተሳተፉ የተለያዩ ሀገራት ኩባንያዎችም የኢትዮጵያን ፈጣን የቴክኖሎጂ ዕድገት አድንቀዋል።
የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የቴክኖሎጂ ሥነ-ምህዳር በመጠቀም ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ጋር እየሰሩ መሆኑን አመልክተዋል።

የቻይና ኩባንያ የሆነው ኒውታክ ሽያጭ ማናጀር ሶፒ ዛኦ ኩባንያው የተለያዩ ጭነቶችን በስካነር የፍተሻ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ኩባንያው ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመሆን በተለያዩ ድንበሮች ላይ ኮንቴነሮችን በስካነር የመፈተሽ ስራ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
እንዲ አይነት ቴክኖሎጂዎች የሀገራትን ስማርት ሲቲ ግንባታ እንደሚያፋጥኑና አገልግሎታቸውን ፈጣንና ዘመናዊ ለማድረግ ወሳኝ መሆናቸውንም አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ስማርት ሲቲ ለመገንባትና አገልግሎቶችን ለማዘመን እያደረገችው ያለውን ጥረትም አድንቀዋል።

ወተር ፎል የተባለው አለም አቀፍ ኩባንያ ሽያጭ ማናጀር ናደር ባዳዲ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ በርካታ ወጣቶች ያላቸውን የቴክኖሎጂና የፈጠራ አቅም በቀላሉ መረዳት ችያለሁ ብለዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀገሪቱ በብዙ ዘርፎች ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበች መሆኑን አንስተው ለዚህ ደግሞ የቴክኖሎጂ ተደራሽነትን ለማስፋት ያደረገችው ጥረት ተጠቃሚ አድርጓታል ነው ያሉት።
የቻይና ኩባንያ የሆነው ኒውታክ ሽያጭ ማናጀር ሶፒ ዛኦ በኢትዮጵያ የረጅም ዓመት የስራ ቆይታ ማድረጋቸውን አስታውሰው በየጊዜው እየታየ ያለውን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዕድገት አድንቀዋል።

የክላውድ ኮምፒዩተርና ዳታ አገልግሎት የሽያጭ ዳይሬክተር ሊዊስ ሊዮ ኩባንያቸው ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በሲም ካርድ አስተዳደር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ደግሞ በተማሪዎች መረጃ አያያዝ ሲስተም ላይ በጋራ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ የተለያዩ አገልግሎቶችን በዲጂታል በመታገዝ ለመስጠት የምታደርገው ጥረት የዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ አገልግሎቶቸን ያቀላጥፋል ብለዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026