
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 15/2017(ኢዜአ)፦ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስጠብቅ በሥነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ የማፍራት ስራን አጠናክረው ማስቀጠል እንደሚጠበቅባቸው የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) ገለጹ።
''ትውልድ በመምህራን ይቀረፃል፤ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል'' በሚል መሪ ሃሳብ ሀገራዊ ለውጡ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችንና የቀጣይ ሀገራዊ ትኩረት መስኮችን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ውይይት ተካሂዷል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት በሀገራዊ ለውጡ ማግስት በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ መስኮች ስኬት ማስመዝገብ ተችሏል።

በዩኒቨርሲቲው የውይይቱ ተሳታፊ ምሁራን የሚቀርቡ ሃሳቦችም በቀጣይ የልማት አቅጣጫዎች ላይ በግብዓትነት እንደሚውሉ አስታውቀዋል።
ይህም ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ለምትገኘው ለውጥም የምሁራን ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በዚህም በምዕራፍ አንድና ሁለት ተግባራዊ የተደረገው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሁሉም የማክሮ አመላካቾች ስኬት ማስመዝገብ እንደተቻለ አስረድተዋል።
በማህበራዊና የኢኮኖሚ የልማት ስራዎች እንዲሁም በዲፕሎማሲው መስክ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ያማከሉ ስኬታማ ስራዎች ውይይት እንደተደረገባቸም ጠቅሰዋል።
በውይይቱ ምሁራን ለሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች መፍትሄ አመላካች የጥናትና ምርምር ስራን ማጠናከርና ለፖሊሲ ግብዓት እንዲውሉ ሚናቸውን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል።
በቀጣይም ምሁራን በዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ፣ በሥነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ በማፍራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስጠብቅ ዜጋ ማፍራት ላይ ይበልጥ ማተኮር እንዳለባቸው ነው የገለጹት።
ሀገር ወዳድ፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን በማጎልበት ዴሞክራሲያዊ ዜጋን የማፍራት ሚናቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም አስረድተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ምሁራንም በሀገራዊ ለውጡ ማግስት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና ዲፕሎማሲ ተግባራዊ የማሻሻያ እርምጃዎች ለሀገር ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማዋል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
በቡና የወጪ ንግድ ምርት መጠንን በመጨመር በኩል የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው፣ እሴትን ጨምሮ ለገበያ መላክ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

ከተሞችን አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ከማድረግ አንጻር ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም አዲስ አበባ ከተማን በኮሪደር ልማት በማስዋብ የተሰራው ስራ ትልቅ ለውጥ መሆኑን ምሁራኑ ገልጸዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026