አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2017(ኢዜአ)፦ መንግስት ባመቻቸላቸው የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውን በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ከስደት ተመላሾች ገለጹ፡፡
አቶ ካሳሁን ለገሰ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ ኑሯቸውን ለማሻሻል በማለም በስደት የተሻለ ነው ወዳሉት ሀገር አቀኑ፡፡
ነገር ግን ሕይወትን ለማሸነፍ የመረጡት መንገድ እንዳሰቡት ሳይሆን ቀርቶ ለ11 ዓመታት ኑሮ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኖባቸው በሰው ሀገር ላይ መከራ ሲገፉ መግፋታቸውን ያስታውሳሉ፡።
"የሰው ወርቅ አያደምቅ" የሚለውን ብሂል በመገንዘብ ውሳኔ ላይ በመድረስ ማቄን ጨርቄን ሳይሉ ወደ ሀገራቸው የተመለሱባትን ቀን ሁልጊዜም ያመሰግኗታል፡።
ከህገ ወጥ ስደት መልስ መንግስት ባመቻቸላቸው የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸው አሁን ላይ የኔ የሚሉትን ጥሪት መቋጠር ጀምረዋል።
በዚህም በእንስሳት ተዋፅዖ አቅርቦት ንግድ ላይ ስራ ተሰማርተው ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጸው፤ መንግስት ከስደት ተመላሽ ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው እንዲለወጡ የሚያደርገው ድጋፍ ለስራቸው ትልቅ ሚና እንዳለውም ይናገራሉ።
መንግስት የመስሪያ ቦታና የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ማድረጉ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር እንዲችሉ ማድረጉንም ገልጸዋል።
የአቶ ካሳሁኑ ውጣ ውረድ ለአብነት ተነሳ እንጂ መንግስት ባመቻቸላቸው የስራ አድል በመጠቀም በሀገራቸው ሰርተው መለወጥ የቻሉ በርካታ ከስደት ተመላሾችን ማንሳት ይቻላል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የካ እና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ሌሎች ከስደት የተመለሱ ዜጎችም መንግስት ባመቻቸላቸው የስራ እድል ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል።
ከ15 ዓመታት በስደት የኖረችው ፍቅርተ አባይነህ በበኩሏ የድካሟን ያህል ምንም ጥሪት ሳትቋጥር ወደ ሀገሯ መመለሷን ተናገራለች።
ወደ ሀገሯ ከተመለሰች በኋላ መንግስት ባመቻቸው የመስሪያ ቦታና የግብዓት አቅርቦት በመታገዝ የባልትና ውጤቶችን በማዘጋጀት መሸጥ መጀመሯን ነው የገለጸችው።
ሌላኛዋ ከስደት ተመላሽ ወይዘሮ አለይካ ናስር በበኩላቸው በሀገሬ ውስጥ ይህን መሰል እድል መኖሩን ባውቅ ልጆቼንና ቤተሰቦቼን ትቼ ስደትን ምርጫዬ አላደርግም ነበር ብለዋል።
ከስደት ተመላሾቹ መንግስት ባመቻቸላቸው እድል በመጠቀም ቤተሰባቸውን ማስተዳደር መቻላቸውን ተናግረዋል።
ወይዘሮ ጸጋ የሺጥላ በህገወጥ መንገድ ከሀገር ተሰደው ባሳለፉት አጭር ጊዜ በርካታ ችግሮችን ማለፋቸውን በማስታወስ በሀገሬ በነፃነት ሰርቼ በገንዘብ የማይታመን ደስታን ማግኘት ምርጫዬ አድርጊያለሁ ትላለች።
አስተያየት ሰጪዎቹ በመንግስት በተመቻቸው እድል ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸውን መምራትና ለሌሎች የስራ እድል መፍጠር በመቻላቸው ምስጋና አቅርበዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር የስራና ክህሎት ቢሮ የስራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክተር ሰብሃዲን ሱልጣን፤ ቢሮው የስራ አጥነት ችግርን ለመፍታትና አካታች የስራ እድሎችን ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ቢሮው ከስደት ተመላሾችን በማሰልጠን የስራ እድል እየፈጠረ መሆኑን አንስተው በ2017 በጀት አመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ 1ሺህ 95 ከስደት ተመላሾች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025