ሌሞ-ጌንቶ፤ ግንቦት 18/2017(ኢዜአ)፦ የኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴን በመከተልና የምርት ማሳደጊያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርታማነታቸውን በእጥፍ ማሳደጋቸውን በደቡብ ኦሞ ዞን የማሌ ወረዳ ከፊል አርብቶ አደሮች ገለፁ።
ከፊል አርብቶ አደሮቹ ከሚያዘወትሩት የከብት እርባታ ባሻገር በእርሻ ስራ ላይ በመሰማራት የገቢ አቅማቸውን እያጎለበቱ ይገኛሉ።
በማሌ ወረዳ በአሸከር ቀበሌ በጥምር ግብርና ስራ የተሰማሩት ከፊል አርብቶ አደር ናስር ዶቄ ለኢዜአ እንዳሉት፥ በአከባቢው ከተለመደው የከብት እርባታ ባሻገር የግብርና ስራዎችን በስፋት እያከናወኑ ይገኛሉ።
በዘንድሮ የበልግ እርሻ በቆሎ፣ ማሽላ እና የጓሮ አትክልቶችን በኩታ ገጠም እያመረቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሰብል ልማቱን ውጤታማ ለማድረግም ምርጥ ዘርና ማዳበሪያን መጠቀማቸው የተሻለ ምርት እንዲያገኙ እያገዛቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ሌላው የወረዳው ነዋሪ ፍርዴ ጋልሻ በበኩላቸው በኩታ ገጠም እርሻ ጉልበትና ጊዜያቸውን በማቀናጀት ሰብሎች በተባይና በነፍሳት እንዳይበሉ የመቆጣጠር ስራ እያከናወኑ መሆኑን አንስተል።
እንዲሁም መንግስት የሚያቀርባቸውን የሰብል ዝርያዎችንና የምርት ማሳደጊያ ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ በመጠቀማቸው በእርሻ ስራቸው ተስፋ ሰጪ ውጤት መመልከት መጀመራቸውን ገልጸዋል።
ወይዘሮ ሽሮ አበራ በበኩላቸው በማህበር በመደራጀት በጀመሩት የእርሻ ስራ የገቢ ምንጫቸውን እያሰፉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ምንላርገው አዲሱ በዞኑ ምርታማነትን ለማሳደግ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በተመለከተ ለአርሶና አርብቶ አደሮች በማስተማር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አርብቶ አደሮች ከከብት እርባታ ባሻገር አትክልትና ፍራፍሬዎችን በስብጥር ማልማት እንዲችሉ፣ አነስተኛ ኩሬዎችን በማዘጋጀት አሳ የሚያረቡበትን እንዲሁም የእንስሳት መኖዎችን በማልማት ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል እና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አድማሱ አወቀ እንዳሉት የማሌ ወረዳ ከፊል አርብቶ አደሮች ከከብት እርባታ ባሻገር በእርሻ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ኑሯቸውን ለማሻሻል እየተጉ ናቸው።
ለውጤታማነቱም የዘር ብዜትና ቴክኖሎጂ የማላመድ ስራዎችን ጨምሮ ምርጥ ተሞክሮዎችን የማስፋፋት ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን ጠቅሰው በአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን ወደ ኢኮኖሚ ምንጭነት ለመቀየር ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዘንድሮው የበልግ አዝመራ ከ900 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር የተሸፈነ ሲሆን ከ77 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ግብርና ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025