የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢንስቲትዩቱ የቆዳ ፋብሪካዎችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን መቅረፍ ይገባዋል- ቋሚ ኮሚቴው

May 27, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንቦት 18/2017(ኢዜአ)፦የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የቆዳ ፋብሪካዎችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማረም ላይ መስራት እንዳለበት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።

ቋሚ ኮሚው የአምራች ኢንዱስትሪ ኢንስቲትዩት የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ምርምር ልማት ማዕከል የ2014/2015 በጀት አመት የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ ውይይት አካሂዷል።

በዚህ ወቅት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሰረት ዳምጤ እንደገለጹት ተቋሙ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የክዋኔ ኦዲት ግኝት ቀርቦበት እንደነበረ አስታውሰዋል።

ከቀረቡበት የኦዲት ግኝቶች ውስጥ ክፍተቶችን ለማሻሻል የሄደበት ርቀት ጥሩ ቢሆንም ቀሪ እርምጃዎችን የሚጠይቁ ተግባራት መኖራቸውን አንስተዋል።

በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ የሚታየውን ክፍተት ከመቅረፍ አንጻር በቀጣይ መስራት እንደሚገባው አመልክተዋል።

የቆዳ ፋብሪካዎች ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ የምርት ስብጥርን የሚጨምሩ ተግባራት ላይ ክፍተቶች መኖራቸውን አንስተው፤ በዚህ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

የምርምር ስራን በማጠናከር ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በዘርፉ ከመፍጠር አንጻር ከአጋር አካላት ጋር መስራትን እንደሚገባውም የኦዲት ግኝቱ እንደሚያሳይ አስታውቀዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በዚህ ወቅት የቆዳና ሌጦ ዘርፍ ትልቅ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል መሆኑን አንስተዋል።

ይህንንም ተከትሎ በዘርፉ ስርነቀል ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ስራዎች ባለፉት አመታት መከናወናቸውን አስታውቀዋል።

የኦዲት ግኝቱን በመውሰድ በትኩረት መሰራቱን አንስተው በቀጣይ ባልተስተካከሉት ላይ እርምት ለማድረግ ይሰራል ብለዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተሩ ሚልኬሳ ጀገማ በበኩላቸው ተቋሙ የተሰጠውን የኦዲት ግኝት ተከትሎ በርካታ የማስተካከያ ተግባራትን ማከናወኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም ቀሪ ክፍተቶችን የማስተካከያ ስራዎች እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አራሬ ሞሲሳ በሰጡት ማጠቃለያ ዘርፉን ውጤታማ ከማድረግ አኳያ ሰፊ ስራ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።

ተቋሙ የድርጊት መርሃ ግብር እስከ ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓም ድረስ መላክ እንዳሚገባው እና በየሶስት ወር የደረሰበትን ማሳወቅ እንዳለበትም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025