የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ጋር ተወያዩ

May 28, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2017(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ጋር የሁለቱን ሃገራት የኢንቨስትመንት ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

መሪዎቹ በመተግበር ላይ ያለውን የትብብር አፈፃፀም በመገምገም በባለብዙ ወገን እንዲሁም አዳዲስ የትብብር መስኮችን በተሻሻለ የኢንቨስትመንት መጠን ለመከወን የሚቻልባቸው ጉዳይች ላይ ተወያይተዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ የጣሊያን መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ትብብሮችን ለማጠናከር ሰርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥቅምት 2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ ወደ ኃላፊነት በመጡ በአጭር ጊዜ በሮም በመገኘት በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የሰላም እና ፀጥታ እንዲሁም በልማት ረገድ ጣልያን ለኢትዮጵያ ልማት የምታደርገውን ድጋፍ አስመልክቶ ውይይት ተደርጎ ነበር።

ከዚህ ውይይት በኋላም መሪዎቹ ጠንካራ የስራ ግንኙነት የመሠረቱ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ በ2016 ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።

ቀጣይ ውይይቶችም በጣሊያን እንዲሁም ሌላ ሀገራት ላይ በተካሄዱ ባለብዙ ወገን መድረኮች ተካሂደዋል።

ጣሊያን የኢትዮጵያ ልማት ቁልፍ አጋር ስትሆን በኢንደስትሪ ብሎም እንደ ጤና፣ ግብርና እና ባሕላዊ ቅርስ ጥበቃ የረጅም ዘመን ደጋፊም መሆኗም ተገልጿል።

የጣሊያን ኩባንያዎች እና የጣሊያን የልማት ትብብር ተቋም ሥራዎችን በንቃት እየደገፉ እንደሚገኙም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሁለቱ መሪዎች በመጨረሻ ስብሰባቸው ለዘላቂ ልማት እና የተሻሻለ ኢንቨስትመንት ያላቸውን የጋራ ርዕይ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026