
አሶሳ፤ ግንቦት 20/2017(ኢዜአ):- የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ዘርፉን የማዘመን ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ሚኒስትሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ስራ የጀመሩትን 24 ስማርት ኮሙኒኬሽን ማሳላጫ ክፍሎች በአሶሳ ከተማ ተገኝተው ዛሬ አስጀምረዋል።

ያስጀመሩትም የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች በ10 የፌዴራል ተቋማት፣ በሁሉም ክልሎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች መሆኑም ተገልጿል።
የኢኖቪሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት፤ መንግስት የቴክኖሎጂ ዘርፉን በማዘመን ዜጎች የተቀላጠፈ እና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ ነው ።
የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በቀላሉ እንዲገናኙና ስራቸውን እንዲያሳልጡ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ይህም ወጪ እና ጊዜን የሚቆጥብ እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ልምድን የሚያዳብር ነው ብለዋል።
የስማርት የኮሙኒኬሽን ማሳላጫ ክፍሎቹ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የያዙ የድምጽ እና የቪዲዮ ፕላትፎርም ያላቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች ስራ መጀመር ኢትዮጵያ ለያዘቸው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አንዱ ማሳያ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ በቀጣይም ዘርፉ በሀገር ሁለንተናዊ ጥቅም የሚኖረውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የስማርት ኮሙኒኬሽን ማሳላጫ ክፍሎችን በጥንቃቄ መጠቀም እና ከወቅቱ ጋር በሚዛመዱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ማዘመን እንደሚገባ አሳስበዋል።
በማስጀመሪያ መረሃ ግብር ላይ የሚኒስቴሩ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026