የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ስማርት የኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍሎች ቀልጣፋ እና ውጤታማ የስራ ተግባቦት እንዲፈጠር የሚያስችሉ ናቸው-ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)

May 30, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንቦት 20/2017(ኢዜአ)፡-ስማርት የኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍሎች ቀልጣፋ እና ውጤታማ የስራ ተግባቦት እንዲፈጠር የሚያስችሉ መሆናቸውን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ገለጹ።


በ10 የፌደራል ተቋማት፣በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የተገነቡ ስማርት የኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍሎች ተመርቀው በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።


የስማርት ኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍሎቹ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ያሉ ባለድርሻ አካላትን በቀላሉ እንዲገናኙና ስራቸውን እንዲያሳልጡ የሚያስችሉ ናቸው።


በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ይህንን ስኬት እንዲመዘገብ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።


ስማርት የኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍሎቹ ለመረጃ ልውውጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተናግረዋል።


ማዕከላቱ ውጤታማ የስራ ግንኙነት እንዲፈጠር በማድረግ አስፈላጊ የሆነ ፈጣን ተግባቦት እንዲፈጠር የሚያግዙ መሆኑን ገልጸዋል።


ለአመራር ሰጭ አካላትም ፈጣን የሆነ ውሳኔ ለመስጠትም ያስችላሉ ነው ያሉት።


በቀጣይም እነዚህን ማዕከላት በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስማርት የኮሙኒኬሽን ስርዓትን ለማጠናከር አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።


በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስራ አስፈጻሚ ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ማዕከላቱ ውጤታማ የዲጅታል ኮሙኒኬሽን ስርዓትን መፍጠራቸውን አንስተዋል።


እንዲሁም ሀገራዊ የዲጂታላይዜሽን ስራን ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026