የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የስማርት ኮሙኒኬሽን ማሳላጫ ክፍሎች የዲጂታል የአገልግሎትን ለማቀላጠፍ የሚያስችሉ ናቸው-ሚኒስቴሩ

May 30, 2025

IDOPRESS

ሠመራ፤ግንቦት 20/2017(ኢዜአ)፡- ስራ የጀመሩት የስማርት ኮሙኒኬሽን ማሳላጫ ክፍሎች የዲጂታል የአገልግሎት ስርዓት ለማቀላጠፍ የሚያስችሉ መሆናቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ።


በዛሬው ዕለት ሚኒስቴሩ በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ የተገነባውን የስማርት ኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍልን ስራ አስጀምሯል።


በዕለቱ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ(ዶ/ር) እንደገለጹት፥ለአገልግሎት የበቁት የስማርት ኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍሎች የዲጂታል አገልግሎት ስርዓቶችን በመጠቀም የተቀላጠፈ ስራን ማከናወን ይቻላል።


ስራዎችን በቅንጅት በማከናወን በአንድ ማዕከል አገልግሎት በማግኘት የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።


በዚህም ጊዜንና ገንዘብን በመቆጠብ ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያመለከቱት ሚኒስትር ዴኤታው፥የቴክኖሎጂውን አገልግሎት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።


የአፋር ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢንጂነር መሀመድ ሰኢድ በበኩላቸው፥የስማርት ኮሙኒኬሸን ማሳለጫው ጥራት ያለውና አስተማማኝ አገልግሎት የሚሰጥ የቴክኖሎጂ ዘርፍ መሆኑን ተናግረዋል።


ኢንጂነር መሀመድ፥የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቴክኖሎጂውን በማመቻቸቱ ምስጋና አቅርበዋል።


የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች በ10 የፌዴራል ተቋማት፣ በሁሉም ክልሎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ዛሬ ስራ መጀመራቸው ቀደም ሲል መገለጹ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026