የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ያግዛል

May 30, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2017(ኢዜአ)፦የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የላቀ ሚና እንዳለው የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

አዲስ አበባን ስማርት ሲቲ ለማድረግ ከተያዙት እቅዶች መካከል በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዙ ፈጣን አገልግሎቶችን መተግበር አንዱና ዋነኛው ሲሆን የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ደግሞ ለስኬቱ ከፍተኛ አበርክቶ አለው።

ይህን ተከትሎ ቢሮው የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠናን አስመልክቶ በየካ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ- ግብር አካሒዷል።


የቢሮው የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ግሩም አብተው በመርሃ-ግብሩ መክፈቻ ላይ እንዳሉት፤ የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና በዲጂታል ቴከኖሎጂ ብቃት ያለው ዜጋ ለማፍራት ከፍተኛ ሚና አለው ።

የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የተያዙትን እቅዶች ለማሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም ጠቅሰዋል።


የየካ ክፍለ ከተማ ቴክኖሎጂ ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቴዎድሮስ ማስረሻ በበኩላቸው፤ የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠናው ቴክኖሎጂን የተረዳና በብቃት የሚጠቀም ወጣት ለመፍጠር ማስቻሉን ነው የጠቀሱት።

በዚሀም በክፍለ ከተማው 25 ሺህ የሚጠጉ ወጣቶችና የመንግስት ሰራተኞች ስልጠናውን በተመለከተ ግንዛቤ እንዲወስዱ መደረጉን ገልጸዋል።

ወጣቶቹ ስልጠናውን ከመከታተል ባለፈ በተጨባጭ ስራ ፈጣሪና ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን መገንዘብ መቻሉንም ጠቅሰዋል።


ወጣት ይገረም አበራ በኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ድረ-ገጾችን በማበልፀግ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በዳታ ሳይንስና በአንድሮይድ ዘርፎች ክህሎቱን ማዳበሩን ተናግሯል።

ወጣት ማርታ መከተ በበኩሏ ስልጠናው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፎች አዳዲስ እና ዘመናዊ የሆኑ እውቀቶችን የሚያስይዝ መሆኑን ተከትሎ የራሴ የሆኑ ስራዎችን ለመፍጠር አስችሎኛል ብላለች።

ስልጠናው በዋናነት በዘርፉ ስራ ለመፍጠር ከፍተኛ እድል ይዞ መምጣቱንም ወጣቶቹ አስታውቀዋል ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025