
ሐረር፤ግንቦት 21/2017(ኢዜአ)፦በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ብቁ የሰው ሃይል በተደራጀ መልኩ ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።
የአየር ትራንስፖርት ደህንነትን አስተማማኝ በማድረግ፤ዘመናዊና ቀልጣፋ አሰራር ከመዘርጋት አንፃር ኢዜአ በድሬደዋ የምስራቅ ማዕከላዊ ሲቪል አቪየሽን የስራ እንቅስቃሴን ቃኝቷል።
በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ እንዳለ አሰፋ፤ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ይበልጥ እያደገ እና እየዘመነ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ከጊዜው ጋር የሚራመድ ቴክኖሎጂ እና ብቁ የሰው ሃይል አስፈላጊ መሆኑን አንስተው፥ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን በጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።
በአየር ትራፊክ ማኔጅመንት፣በአቪዬሽን ቁጥጥር እና በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ዘመናዊ አሰራሮችና ቀልጣፋ አገልግሎቶች መኖራቸውን አንስተዋል።
በተለይም በሙያ ክህሎት ስልጠና በኩል ከሀገር ውስጥ አልፎ ለሌሎች የአፍሪካ አገራትም ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፥ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው የመሪነት ሚናውን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
የድሬደዋ ምስራቅ ማዕከላዊ ሲቪል አቪዬሽን ተጠባባቂ ሃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ክበበው፥የአየር በረራ ደህንነት በየትኛውም ጊዜና ሰዓት በአስተማማኝ መልኩ እየተጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል።
ለዚህም አስተማማኝ ቴክኖሎጂና በብቃት የሰለጠነ የሰው ሃይል መኖሩን ጠቅሰው፥ በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።
የድሬደዋ ምስራቅ ማዕከላዊ ሲቪል አቪዬሽን የበረራ ቅኝት ምህንድስና ቴክኒሻን ሄኖክ ሚካኤል በበኩላቸው፥ የአየር በረራ ደህንነቱ በተጠበቀና በተሳለጠ መልኩ የክትትልና ቁጥጥር ስራው በአስተማማኝ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የአየር በረራ ደህንነት የተሳለጠ እንዲሆን በኮሙኒኬሽን ግንኙነት ዘርፍ 24 ሰዓት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጸችው ደግሞ መሰረት ታከለ ናት።
የዘርፉ ባለሙያ የሆኑት መሰረት ታከለ እና የአፕሮች የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ የሆነው ጌቱ ኑርም፤ ለበረራ ደህንነት በልዩ ትኩረትና ጥንቃቄ በማገልገል ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026