
ሚዛን አማን፤ግንቦት 27/2017 (ኢዜአ)፦በሚዛን አማን ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ እንዲፋጠን ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ።
ከነዋሪዎቹ መካከል መቶ አለቃ ተስፋዬ ናትናኤል፥ የከተማዋን ገጽታ እየቀየረ ያለውን የኮሪደር ልማት የእግረኛን መንገድ በማስፋትና የመናፈሻ አገልግሎትን ማስፋት ያሰቻለ ሰው ተኮር ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
ልማቱ በተሳካ ሁኔታ እንዲፋጠን ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ አስታውቃዋል።
እስከ አሁን የተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ስራዎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴን በማቀላጠፍ የተሽከርካሪ አደጋን መቀነስ እንደሚያስችል አስተያየቱን የሰጠው ደግሞ ሌላው የከተማው ነዋሪ ወጣት ታከለ ገብረማሪያም ነው።
ከተማዋን ንጹህ፣አረንጓዴና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ የተጀመረው የኮሪደር ልማት በተሳለጠ ሁኔታ እንዲፋጠን የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያጠናክር ተናግሯል።
ወጣት ኤርሚያስ አበበ በበኩሉ፥የከተማዋ የኮሪደር ልማት ሥራን በፍጥነት ለማጠናቀቅ በሚደረገው ርብርብ ድጋፉን እንደሚቀጥል ገልጿል።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ሰሎሞን ሌዊ ፤ በከተማዋ ከተጀመረው የአንድ ኪሎሜትር የኮሪደር ልማት ስራ የጎርፍ መፋሰሻ፣ የአረንጓዴ ልማት እና የእግረኛ መንገድ ስራው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ብለዋል።
በኮሪደር ልማት ሥራ ኅብረተሰቡ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰው፥የተጀመሩትን በቅርብ ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ቀጣዩን የኮሪደር ልማት ምዕራፍ ለማስጀመር ከከተማው ኅብረተሰብ ጋር በመቀናጀት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026