
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 28/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ለምትተገብራቸው አሰራሮች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት(ፋኦ) ገለጸ።
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ድርጅት የቴክኒክ አማካሪ ጀምስ ስዊራኒ ለኢዜአ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻል በምታደርገው ጥረት የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ተግባራዊ ያደረገቻቸው አሰራሮች ተጨባጭ ውጤት አምጥተዋል።

በስንዴ ምርታማነት፣ ግብርናውን ለማዘመን ተግባራዊ የተደረጉ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲሁም በዘርፉ የተደረጉ ኢንቨስትመንቶች ዘላቂ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት(ፋኦ) በኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚተገበሩ መርሃ ግብሮችን ለመደገፍ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ምርትን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማምረት ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራትን እንደሚደግፍም ነው ጀምስ ስዊራኒ የገለጹት።

ድርጅቱ የግብርናና የእንስሳት ጤናና ምርታማነትን ለማሳደግ ተግባራዊ ለሚደረጉ አሰራሮች የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ድርጅቱ ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻል ተግባራዊ ያደረገቻቸውን የሌማት ትሩፋት፣ አረንጓዴ አሻራና ሌሎች መርሃ ግብሮችን በስፋት እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል።
የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ላስመዘገበችው ውጤት እውቅና መስጠቱን አስታውሰው በቀጣይም የበለጠ ውጤት እንደምታስመዘግብ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026