
ሀዋሳ፤ግንቦት 28/2017 (ኢዜአ)፦አመራሩ በክልሉ የተመዘገቡ ውጤቶችን በብቃትና በቁርጠኝነት መምራትና አጠናክሮ ለማስቀጠል መረባረብ እንደሚገባው ተገልጿል።
“ብቁ አመራር መገንባት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ በሲዳማ ክልል ለሚገኙ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በሀዋሳ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በዚህም በሲዳማ ክልል የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ ብቃት ባለው አመራር የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል መረባረብ እንደሚገባ ተመላክቷል።
በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሀም ማርሻሎ በወቅቱ እንዳሉት፥ በክልሉ የቤተሰብ ብልጽግናን ለማምጣት የተጀመረው ስራ ስኬታማ እንዲሆን አመራሩ በብቃትና በቁርጠኝነት መምራት እንዳለበትም ተናግረዋል።
በአገር አቀፍም ሆነ በክልል ደረጃ አመራሩ ማህበረሰቡን በማስተባበር የተመዘገቡ ውጤቶችና የመጡ ለውጦች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መትጋት ይገባዋል ብለዋል።
በክልል ደረጃ የቤተሰብ ብልጽግናን ለማምጣት 68 ፓኬጆች ያሉት 8 ኢንሺዬቲቮች ተቀርጸው ወደ ተግባር መገባቱን የገለፁት ኃላፊው ከኢንሼቲቮቹ አንዱ በሆነው በሌማት ትሩፋት በተለይም በዶሮና የወተት ላም እርባታ፣ በንብ ማነብና በዓሳ እርባታ ረገድ ውጤታማ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ስልጠና ላይ ከክልል እስከ ዞን ያሉ ከፍተኛ አመራር አባላት እየተሳተፉ ይገኛል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026