ባህርዳር፤ግንቦት 28/2017(ኢዜአ)፦በክልሉ ነግዶ ለማትረፍም ሆነ ሰርቶ ለመለወጥ ምቹ ሁኔታ የፈጠረውን ሰላምን በዘላቂነት ለማፅናት ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ በአማራ ክልል የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ።
"ለሁለንተናዊ ብልፅግና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ክልል አቀፍ የንቅናቄ መድርክ በባህርዳር ተካሂዷል።
ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል በክልሉ ሃብሩ ከተማ የመጡት የንግዱ ማህበረስ አባል ሻለቃ መስፍን ነግሶ በሰጡት አስተያየት፥ሰርተን ለመለወጥ ሁላችንም በቅድሚያ ለሰላሙ ዘብ ልንቆም ይገባል።
የፅንፈኛውን ቡድን የጥፋት ድርጊት እንደሚያወግዙ ያነሱት ሻለቃ መስፍን ፤ በህግ ማስከበሩ እርምጃ የተኘውን ሰላም አፅንተን ማስቀጠል ይጠበቅብናል ብለዋል።
እኔም ሰላሙ ተከብሮ ልማቱ እንዲፋጠን ግብርን በወቅቱ ከመክፈል ጀምሮ የሚጠበቅብኝን ሁሉ እወጣለሁ ሲሉ አስታውቀዋል።
ሌላው የንግዱ ማህበረሰብ አባል የሆኑት የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ክቡር ጌታቸው በበኩላቸው፥ነግዶ ለማትረፍና ለመለወጥ ሰላምን አብዝተን ልንሰብክና ለማጽናት መስራት አለብን ብለዋል።
በከተማዋ እየተካሄደ ያለውን የኮሪደር ልማት የንግዱ ማህበረሰብ እየደገፈ እንደሚገኝ አንሰተው፤በቀጣይም የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል አስታውቀዋል።
ሰላምን ለማፅናት መንግስት የጀመረውን ውይይት አጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት ደግሞ ከደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ ንፋስ መውጫ ከተማ የመጡት ወይዘሮ መሰረት ብርሃን ናቸው።
እኛም ፅንፈኝነትን አምረን በመታገል የንግድ እንቅስቃሴው እንዲነቃቃና ልማቱ እንዲፋጠን የሚጠበቅብንን ሁሉ ሃላፊነት ልንወጣ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
ነግዶ ለማትረፍም ሆነ ሰርቶ ለመለወጥ ምቹ ሁኔታ የፈጠረውን ሰላምን በዘላቂነት አፅንቶ ለማስቀጠል ከመንግስት ጎን ተሰልፋው ድጋፋቸውን በማጠናከር የድርሻቸውን እንደሚወጡ አባላቱ ተናግረዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) እንዳመለከቱት፤ ያለሰላም ልማትና ዕድገትን ማረጋገጥ አይቻልም።
ልማቱን ለማፋጠንም ሆነ የሀገሪቱን ዕድገት ማስቀጠል የምንችለው ፅንፈኝነትን በጋራ አምርረን መታገልና ሰላምን በዘላቂነት ማረጋገጥ ስንችል ነው ብለዋል።
ጽንፈኛውን ከክልሉ በማፅዳት ሰላምን አጥብቆ ለማስቀጠል የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ሰላምና ልማትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።
የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢብራሂም መሀመድ (ዶ/ር) ፤ የኑሮ ውድነትና ህገወጥ ንግድን ለመከላከል የንግዱ ማህበረሰብ ከመንግስት ጎን ሆኖ በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት፣ግብርናና ገቢዎች ቢሮ በጋራ ባዘጋጁት ክልል አቀፍ የንቅናቄ መድረክ ላይ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025