
አዲስ አበባ፤ግንቦት 28/2017(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ ልማቶች የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትና የቱሪስትን ፍሰትን የሚጨምሩ መሆናቸውን ኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ትረስት ፈንድ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር በከተማው የተሰሩና እየተሰሩ ያሉትን ሰው ቶኮር ልማቶች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በአየር መንገዱ የሰራተኞች ተግባቦትና የውስጥ ኮሙኒኬሽን ማናጀር አቶ ሰለሞን ገብረመድን በጉብኝቱ ወቅት፤ አየር መንገዱ በየዓመቱ የሰራተኞችን ቀን እንደሚያከብር አስታውሰው፤ ዘንድሮም ሳምንቱን ሙሉ በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር ታቅዶ እየተከበረ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
የዛሬው ጉብኝትም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ሰራተኞቹ በከተማው ውስጥ ያሉ ልማቶችን ተገንዝበው በሄዱበት ዓለም ዳርቻ ሁሉ ሀገራችንን ለማስተዋወቅ የድርሻችንን እንድንወጣ ያለመ ነው ብለዋል ፡፡
በጉብኝቱም ተጠናክሮ ሊቀጥሉ የሚገቡ አስደማሚ ልማቶች መመልከታቸውንም ገልጸዋል ፡፡
አየር መንገዱ ከከተማ አስተዳደሩ የማህበራዊ ትረስት ፈንድ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር የተለያዩ ሰው ቶከር ልማቶችን እየደገፈ መሆኑንና ይህንም አጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ነው የገለጹት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ አስራት ንጉሴ በበኩላቸው ፤ የከተማው ነዋሪና ሁሉም ዜጋ በከተማው ልማት ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስችል ተግባር እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት የማቋቋም ተግባርም እያተከናወነ መሆኑን አክለዋል፡፡
በዛሬው ጉብኝት የአየር መንገዱ ሰራተኞች በከተማው ውስጥ የሚሰሩ ልማቶች ላይ ግንዛቤ የፈጠረና በሰው ተኮር ልማት ላይ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ግንዛቤ የተፈጠረበት ነው ብለዋል ፡፡

በአየር መንገዱ የአቬየሽን ዩኒቨርርሲቲ የፓይለት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ኃላፊ ካፒቴን አብርሃም አከለ ፤ አዲስ አበባን ከዓለም አቀፍ ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ልማቶች መገንዘቡን ተናግሯል፡፡
በከተማው በተሰሩ የኮሪደር ልማቶች፣ ሕብረተሰቡን የሚጠቅሙ መዝናኛዎችና በሰው ተኮር ልማቶች መደመማቸውን የገለጹት በአየር መንገዱ የሰው ሃብት ክፍል ባለሙያ ወይዘሮ ቅድስት ጌታሁን ናቸው ፡፡

በከተማው የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ ልማቶች ከተማዋን ለነዋሪዋቿ ምቹና ፅዱ የሚያደርግና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ትልቅ ድርሻ ያለው የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር የሚያደርግ ነው ብለዋል ፡፡
በመርሃ ግብሩም አየር መንገድ ሰራተኞች መኖሪያ ህንጻ ግንባታ የደረሰበት ደረጃ፣ የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል፤ የኮሪደር ልማት መንገዶች፣ መዝናኛዎች፣ የመኪና ማቆሚያ ህንጻ፣ ተስፋ የአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች ምገባ ማዕከልን ጎብኝተዋል ።

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026