አዲስ አበባ፤ ግንቦት 29/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያን ከተረጂነት ሙሉ ለሙሉ በማላቀቅ ራሷን እንድትችል የተያዘው ግብ እንዲሳካ ኢትዮጵያውያን በላቀ ትጋት እንዲሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስገነዘቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ልዩ ቆይታ ተረጂነት የኢትዮጵያ አደገኛ ስብራት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ራስን ከመለወጥ ይልቅ ሌሎችን በመለመንና በመጠበቅ መኖር ትልቅ የስነ-ልቦና ስብራት መሆኑንም አመልክተዋል።
ኢትዮጵያን የሚያክል ትልቅ ሀገር ራሷን መመገብ እና ራሷን መቻል አቅቷት ሌሎችን መለመኗ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው ብለዋል።
እኛ ተረድተን ተረጂነትን ማውረስ የለብንም እኛ ለምነን ልመናን ማሸጋገር የለብንም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተረጂነት እኛ ጋር መቆም አለበት ሲሉም ገልጸዋል።
መንግስት ተረጂነት የፈጠረውን ከፍተኛ ስብራት በመጠገን ከተረጂነት መውጣት ብቻ ሳይሆን ረጂ በመሆን ለውጥ ማምጣት አለብን የሚል ጽኑ አቋም መያዙንም ተናግረዋል።
ይህንን ከግምት በማስገባትም እስከ ታችኛው የአስተዳደር እርከን በመውረድ በጉዳዩ ላይ ከህዝብ ጋር ሰፊ ውይይት መካሄዱን ጠቅሰው ከህዝቡ የተገኘው ምላሽ የሚያስደስት እንደነበር ነው ያወሱት።
እንፍጠን፣ እንፍጠር እና እንስራ ይብቃን ልመና የኢትዮጵያውያን የወል ድምጽ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተረጂነት መላቀቅ የመንግስት እና የጋራ አቋም መሆኑን አንስተዋል።
መንግስት እና ህዝብ ከተረጂነት ለመላቀቅ ባከናወኑት ስራ የሚታዩ ተጨባጭ ለውጦች መምጣታቸውን ገልጸዋል።
ለዚህም በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ 27 ሚሊዮን ገደማ ተረጂ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ አሃዝ በ2017 ዓ.ም ወደ 3 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
23 ሚሊዮን ህዝብ ከተረጂነት ማውጣት የኢትዮጵያ ማንሰራራት አንዱ ማሳያ እንደሆነ ጠቅሰው የተገኘው ስኬት ትልቅ ድል መሆኑንም አስረድተዋል።
መንግስት በጥቂት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ከተረጂነት ሙሉ ለሙሉ የማላቀቅ ግብ አስቀምጦ እየሰራ እንደሆነም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ያነሱት።
ከተረጂነት ተላቆ ራስን በመቻል አልፎም ሌሎችን ለመርዳት የተያዘውን ውጥን ለማሳካት ህዝቡ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላለፍዋል።
#Ethiopian_News_Agency
#ኢዜአ #Ethiopia
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025