አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2017 (ኢዜአ)፦ አዲስ አበባፅዱ፣ ውብ እና ለመኖር ምቹ ለጎብኚዎችም ተመራጭ እስከምትሆን ሌት ተቀን መትጋታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር በመሆን ከአንበሳ ጋራዥ-ጃክሮስ እና የጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በመጎብኘት ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
ከአንበሳ ጋራዥ-ጃክሮስ እና የጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ለሕዝብ በገባነው ቃል መሰረት እና ሕዝብን ባሳተፈ መንገድ በተያዘለት ጊዜ መከናወኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
አዲስ አበባፅዱ፣ ውብ እና ለመኖር ምቹ ለጎብኚዎችም ተመራጭ እስከምትሆን ሌት ተቀን መትጋታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት።
የአንበሳ ጋራዥ-ጃክሮስ እና የጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ከስምንት ኮሪደሮች አንዱ መሆኑንም አመልክተዋል።
በኮሪደር ልማቱ የ4 ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ፤ ከ8 ኪሎ ሜትር በላይ ደረጃውን የጠበቀ የእግረኛ መንገድ፤ 3 የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ ስፍራዎች፣ የህፃናት መጫወቻዎች፣ 7 ፕላዛዎች፣ 6 የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች፣ ፋውንቴኖች 13 ታክሲ መጫኛና ማውረጃ ቦታዎች፣ 872 ሱቆች እና የህዝብ ማረፊያ ክፍት ቦታዎች እና የንግድ ቤቶች ያካተተ መሆኑንመ ገልጸዋል።
መስመሩ የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅ የሚታይበት ለአደጋ የተጋለጠና አስቸጋሪ እንደነበር ያወሱት ከንቲባዋ አሁን ላይ የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ በሚያደርግ ሁኔታ ስራው መከወኑንም ነው የገለጹት።
ከመንገድ ዳር ያላቸው ርቀት እና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረገ አካታች መሰረተ ልማቶች መገንባታቸውን አብራርተዋል።
ከጎሮ ዋና መስመር ለሚመጡ ተሸከርካሪዎችና ከቦሌ ዓለም አቀፍ በረራ ተርሚናል በኩል የሚመጡ ተሽከርካሪዎችን በማስተንፈስ ለከተማዋ የትራፊክ መጨናነቅ መፍትሔ እንደሚሰጥም ነው ያስረዱት።
በተጨማሪም በርካታ አነስተኛ የንግድ ስራዎች በአካባቢው መኖራቸው በሺዎች ለሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቋሚ የስራእድል እንዲፈጠር ማድረጉንም ጠቁመዋል።
ሁሌም ህዝብን መሠረት ያደረገ ልማት መስራታችን ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ የምናስረክባት አዲስ አበባ ፅዱ፣ ውብ እና ለመኖር ምቹ እንዲሁም ለጎብኚዎች ተመራጭ እስከምትሆን ሌት ተቀን መትጋታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
የከተማው ነዋሪ ለልማት ስራው እያደረገ ላለው ድጋፍም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025