ነገሌ ቦረና፤ ሰኔ 3/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን የድርቅ ተጋላጭነትን በዘላቂ ልማት ለመቋቋም በ25ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ መከናወኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
በዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት የተፈጥሮ ሀብት ቡድን መሪ ወንዶ ሸርቦቴ፤ ዘንድሮ 267 ተፋሰሶችን መሰረት ያደረገ 25ሺህ 467 ሄክታር መሬትን የሚያካልል የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡
የእርከን ስራ፣ በጎርፍ የተቦረቦሩ መሬቶችን ማልማት፣ የችግኝ ዝግጅት፣ በተደጋጋሚ የተጎዳ የግጦሽ ሳር ልማትና ምንጭ ማጎልበት ዋና ዋና ስራዎች እንደነበሩ ጠቁመዋል፡፡
እስካሁንም 17ሺህ 141 ኪሎ ሜትር የእርከን እንዲሁም በጎርፍ የተሸረሸሩ የመሬት ክፍሎችን የማልማት ስራ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ለበጋ ወራት አገልግሎት የሚሰጡ ምንጮች መጎልበታቸውን፣ የችግኝ መትከያ ጉድጓዶች ዝግጅትም ጎን ለጎን ሲከናወን መቆየቱን ገልጸዋል።
ተፋሰሶቹን በእጽዋት በመሸፈን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ማዘጋጀትም የስራው አካል መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በተፋሰስ ልማት ስራው ከ185ሺህ 200 በላይ ወጣቶች፣ ሴቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
በተያያዘም በዘንድሮ የበጋ ወራት በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች ከ11ሺህ ሄክታር በላይ የግጦሽ ሳር መሬት ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ ተከልሏል ብለዋል፡፡
የተከለለው የግጦሽ ሳር ልማት በበጋ ወራት ለአገልግሎት ክፍት ሲሆን ከ55ሺህ የሚበልጥ የቤት እንስሳትን ተጠቃሚ የማድረግ አቅም ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዞኑ በድርቅ ተጋላጭ ከመሆን እና ከዝናብ እጥረት የሚያጋጥም የመኖ እጥረት በቤት እንስሳት ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ አስታውሰዋል፡፡
ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ችግሩን በዘላቂ ልማት ለመቋቋም በዞኑ ህዝብ ተሳትፎ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ልማት ስራ በመካሄድ ላይ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026