አዲስ አበባ፤ሰኔ 5/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጥያቄ ፍትሃዊ፣ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥና የዜጎቿን የመጪው ዘመን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ሲሉ ምሁራን ገለጹ።
ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ካሉ አገራት በርካታ የህዝብ ቁጥርና በፍጥነት እያደገ የሚገኝ ኢኮኖሚ ባለቤት ብትሆንም የባህር በር ባለቤት አለመሆኗ ዕድገቷ ከዚህ በላይ እንዳይሆን ተገዳድሮታል።
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የባህር በር ያላቸው አገራት ከሌላቸው አገራት በየዓመቱ የሁለት እስከ ሶስት በመቶ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ያስመዘግባሉ።
በዚህም ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት አለመሆን በኢኮኖሚዋ ላይ ከፍተኛ ጫና ከመፍጠሩ ባለፈ ስትራቴጂካዊ ተጽዕኖ እንዳለው ይገለጻል።
በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት መሪ ተመራማሪ አማረ ቀናው (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የባህር በር ጥያቄ ጉዳይ ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በላይ ነው።
ለአንድ አገር ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትና ደህንነት መረጋገጥ የባህር በር ወሳኝና አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን ይጠቅሳሉ።
የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጥያቄ ፍትሃዊ፣የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥና የዜጎቿን የመጪው ዘመን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ሰላማዊ መርህን ተከትላ ያቀረበችው የባህር በር ጥያቄ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ዓለምአቀፍ ተቋማትና በፖሊሲ አውጪዎች አጽንኦት እየተሰጠው መምጣቱንም ነው ያነሱት።
ኢትዮጵያ ለቀይ ባህር ካላት ቅርበት አኳያ በዚያ አካባቢ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በትኩረት ትከታተላለች ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩትም በጉዳዩ ላይ በቂ ገንዛቤ በመፍጠር የመፍትሔ አማራጮችን በማመላከት በኩል ሲሰራ እንደቆየ አንስተዋል።
የኢትዮጵያ የፍትሃዊነትና የህልውና ጉዳይ የሆነው የባህር በር ጥያቄ በቅርቡ ምላሽ የሚያገኝበት ዕድሎች መኖራቸውንም ያብራራሉ።
በመሆኑን የጎረቤት አገራትን ጥቅም ባስከበረና የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ የባህር በር ጥያቄዋ ምላሽ እንዲያገኝ ሰላማዊ የሆነ ግፊት ማድረጓን ትቀጥላለች ብለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ጄይሉ ዑመር (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ ሰጥቶ በመቀበል መርህ የባህር በር የማግኘት ጥያቄ ማቅረቧ ተገቢና አዋጭ መሆኑን ተናግረዋል።
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጉዳዩ ምን ያህል ወሳኝ መሆኑን የሚያመላክቱ ሰነዶችን በጥናትና ምርምር ላይ ተመርኩዘው ማቅረብ አለባቸው ብለዋል።
ከዚያ ባለፈ ትውልዱ ስለ ጉዳዩ በቂ ዕውቀት እንዲኖረው የማስገንዘብ ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከተለያዩ አገራት ጋር የምታደርገው የመሰረተ ልማት ትስስር የወደብ አማራጮችን ማስፋት ጉልህ ሚና እንዳለውም ነው ዶክተር አማረ የገለጹት።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025