የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የኢጋድ አባል ሀገራት የቀጣናውን የደህንነት ስጋቶች የሚመክት የዲጂታል አቅም መገንባት አለባቸው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)

Jun 20, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2017 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት የቀጣናውን የደህንነት ስጋቶች የሚመክት የዲጂታል አቅም እንዲገነቡ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ሳይበር ደህንነት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ሴሚናር በኬንያ ናይሮቢ ተካሄዷል።

“ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ሳይበር ደህንነትን ለፀጥታ፣ ትብብር እና የማይበገር አቅም ግንባታ ያላቸውን ድርሻ ማላቅ” የሴሚናሩ መሪ ሀሳብ ነው።

በሴሚናሩ ላይ የኢጋድ አባል ሀገራት የፀጥታ እና የወንጀል ምርመራ ተቋማት አመራሮች፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ሳይበር ደህንነት ላይ የሚሰሩ የግሉ ዘርፍ ባለሙያዎች እንዲሁም የቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።


የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች፣ ሽብርተኝነት፣ የሳይበር ወንጀል እና የድንበር አስተዳደር ክፍተቶችን ጨምሮ በቀጣናው ውስብስብ የደህንነት ፈተናዎች እንዳሉ ገልጸዋል።

ችግሮቹ ሀገር በቀል የሆኑ የዲጂታል መፍትሄዎችን ለመቅረጽ የሚያስችል እድል ይዘው መምጣታቸውን አመልክተዋል።

የኢጋድ አባል ሀገራት በሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጠራ ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ በቀጣናው በየጊዜው እየተቀያየሩ ያሉ ፈተናዎችን እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል።

በቀጣናው ያሉ ስጋቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ የዲጂታል መፍትሄዎች ላይ መልካም ጅምሮ ቢኖርም አሁንም ብዙ የቤት ስራ ይቀረናል ብለዋል ዋና ፀሐፊው።

የሳይበር ጥቃቶች ከቀጣናው ዋንኛ የደህንነት ስጋቶች መካከል እንደሚቀጠስ ገልጸው ሀገራት የዲጂታል ስርዓታቸውን ማጠናከር፣ የሳይበር አቅማቸውን እና የዲጂታል ክህሎትን መገንባት ላይ አበክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የሳይበር ስጋቶችን ከመመከት ባለፈ ለኢኮኖሚ ልማት ያላቸውንም አቅም አሟጦ መጠቀም እንደሚያስፈልግ ነው ያስገነዘቡት።

ኢጋድ ወጥነት ያለው ቀጣናዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕቀፎች እና የሳይበር ደህንነት የህግ ማዕቀፎች እንዲኖሩ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።


ሁላችንም የቀጣናው መጻኢ የዲጂታል ደህንነት ማዕቀፍ ቀራጮች ነን ያሉት ዋና ፀሐፊው ለዚህም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢጋድ አባል ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ ከለውጡ በኋላ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲ በመቅረጽ፣ ተቋማዊ አደረጃጀት በመፍጠር፣ መሰረተ ልማት በመገንባት እና ዘርፉ የተለያዩ መስኮችን በመደገፍ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም ብሄራዊ ደህንነት፣ ጤና፣ ግብርናን ጨምሮ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመረኮዙ የፈጠራ መፍትሄዎችን እያቀረበ ይገኛል።

በሳይበር ደህንነት ረገድም መንግስት ፖሊሲ በመከለስ፣ ተቋማዊ አቅምን በማጠናከር እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን አከናውኗል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶች በመመከት እና የተቋማትን የሳይበር አቅም በመገንባት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

በተጨማሪም በዘርፎቹ ያሉ የሕግ ማዕቀፎችን በማሻሻል እና ዓለም አቀፍ ትብብርን የማጠናከር ስራም ትኩረት ተሰጥቶታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025