የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የመንግሥት አገልግሎት ሪፎርም ከአጀንዳ 2063 እና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር የተጣጣመ ነው

Jun 24, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የመንግሥት አገልግሎት ሪፎርም ከአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 እና ከመንግስታቱ ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦች ጋር የተጣጣመ መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

ኢትዮጵያ ከሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በትይዩ ያስተናገደቻቸው 10ኛው የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር እና የተመድ የአፍሪካ ቀጣናዊ ፎረም ዛሬ ተጠናቀዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ መድረኮቹ ስኬታማ መሆናቸውን ገልጸዋል።


በዓለም ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን መቋቋምና ቀድሞ ምላሽ መስጠት የሚችሉ ጠንካራ ተቋማትን መፍጠር ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለውን ውስብስብ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ አዳዲስ ፈጠራዎችና ሞዴሎችን ገቢራዊ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት።

የመንግሥት አገልግሎት በአፍሪካ ለዘመናት የቆዩ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል መሆኑን በመጥቀስ፤ በአገልግሎት ሰጭዎች ላይ የክህሎት፣ የአመራርና የትብብር አቅምን ማጎልበት ለአህጉራዊ ሽግግር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ የመንግስት አገልግሎትን ለማዘመን በሪፎርም ላይ መሆኗን ጠቅሰው፥ ለዜጎች ፍትሐዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሶብ የተሰኘ መሰረታዊ ተቋም መገንባቷን ገልጸዋል፡፡

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፅንሰ ሀሳብ ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት የመነጨ መሆኑን ጠቅሰው፤ ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበበት እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ዜጎች የቦታ ርቀት ወይም ሁኔታዎች ሳይገድቧቸው ፍትሐዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት አሰራር መሆኑን አቶ አደም አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የመንግሥት አገልግሎት ሪፎርም አካታች መሆኑን ጠቁመው፤ ከአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 እና ከተመድ 2030 የዘላቂ ልማት ግቦች ጋር የተሳሰረ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት በመፍጠር ተቋማዊ ተጠያቂነትን ማስፈንና የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ልምዶች የተገኙበት መሆኑን ገልጸዋል።

ዲጂታላይዜሽን፣ አቅም ግንባታ እና ፈጠራ የታከለበት አሰራሮች ቀጣይነት ሊኖራቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ(ዶ/ር)፥ አህጉራዊ ጉባኤው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ለዜጎች ፍትሐዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ጠንካራ ውሳኔ ተላልፎበታል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የመንግስት አገልግሎትን በማዘመን ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የተጓዘችበትን ርቀት ታሳቢ በማድረግ ቀጣዩን ጉባኤ በድጋሚ እንድታስተናግድ መመረጧን ገልጸዋል፡፡


በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የአስተዳደር እና ግጭት መከላከል ዳይሬክተር ፔሸንስ ችራድዛ በበኩላቸው፤ በትይዩ የተካሄዱት ሁለቱ ስብሰባዎች በስኬት እንዲጠናቀቁ ላደረጉት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሁለቱ ጉባኤዎች በአፍሪካ የሚስተዋሉ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመለየት የመንግስት ሰራተኞችን ለማበረታታትና ጠንካራ ተቋም ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ መንግስታት ለዜጎቻቸው ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆናቸውን በተግባር ያሳዩበት ሁነት መሆኑን አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025