የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በጎንደር ከተማ እየተከናወነ ላለው የኮሪደር ልማት ሥራ ህብረተሰቡ በተለያየ መንገድ ድጋፉን አጠናክሮ ቀጥሏል

Jun 27, 2025

IDOPRESS

ጎንደር፤ ሰኔ 19/2017(ኢዜአ)፦ በጎንደር ከተማ እየተከናወነ ለሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራ ህብረተሰቡ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት አስተዋጽኦ ማበርከቱን የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አስታወቁ።

ምክትል ከንቲባዋ ወይዘሮ ደብሬ የኋላ ለኢዜአ እንደተናገሩት በህዝቡ የነቃ ተሳትፎና ድጋፍ የኮሪደር ልማቱን በአጭር ጊዜ ወደ ትግበራ በማስገባት ተጨባጭ አፈጻጸም ማምጣት ተችሏል፡፡


ህብረተሰቡ ለመጀመሪያና ለሁለተኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ በገንዘብ፣ በጉልበትና በእውቀት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ገልጸዋል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ ፈጥኖ እንዲጠናቀቅና 2ኛው ዙር እንዲጀመር የነቃ ትብብር ማድረጉንም ነው ያስታወሱት።

የኮሪደር ልማት ሥራ ግቡን እንዲመታ ህብረተሰቡ በመንግስት በተሰጠው ዲዛይን መሰረት ሕንጻና መኖሪያ ቤቱን በራሱ ወጪ በማደስ፤ በመጠገንና ቀለም በመቀባት ለልማቱ ድጋፉን አሳይቷል ብለዋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ እየተከናወነ ለሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በሀገር ውስጥና በውጪ የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆችና ባለሀብቶች የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል።


ከተማው አሁን ላይ ወደ ተሟላና አስተማማኝ ሰላም በመሸጋገሩ ተቀዛቅዞ የቆየው የከተማው የንግድ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ መነቃቃት አሳይቷል፡፡

ከፒያሳ ኮሌጅ ማዞሪያና አዘዞ አየር ማረፊያ የእግረኛና የብስክሌት መንገድ፣ የአረንጓዴ መናፈሻዎች እንዲሁም ሌሎች ግንባታዎችን አካቶ እየተከናወነ ያለው 2ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ 12 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ሥራው በምሽት ጭምር በመስራት የህዝቡን የሥራ ባህል መቀየሩን ገልጸው፣ ልማቱ ለበርካታ ወገኖች የሥራ ዕድል መፍጠር ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡

በተያዘው ሳምንት በጎንደር ከተማ እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከመላ ሀገሪቱ በተውጣጡ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና አመራሮች መጎብኘቱ የሚታወስ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026