የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲዋን ማጠናከር የሚያስችል ውጤታማ ተሳትፎ አድርጋለች

Jun 27, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2017(ኢዜአ)፦ በአንጎላ አዘጋጅነት በተካሄደው የአፍሪካ አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲዋን የሚያጠናክር ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

17ኛው የአፍሪካ አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ በትናንትናው ዕለት ተጠናቋል።

ጉባኤው ኢትዮጵያ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ጋር የተሰናሰነውን የቢዝነስ ዲፕሎማሲዋን ያጠናከረችበት መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዘርይሁን አበበ ለኢዜአ ገልጸዋል።


በጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይቶች ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ከአንጎላው ፕሬዝዳንትና ከወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ-መንበር ጆ ሌሬንሶ፤ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቦሎስና የአፍሪካ ኮርፖሬት ካውንስል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሎሪ ሊዘር ጋር መወያየታቸውንም ጠቅሰዋል።

ከዋናው ጉባኤ ጎን ለጎን በነበሩ የተለያዩ መድረኮች ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴን ጨምሮ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ(ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) በኩል ተሳትፎ በማድረግ የኢትዮጵያን አቋም ማንጸባረቅ ተችሏል ብለዋል።

በዚህም በተለይም ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኗን ያሳየችባቸው፣ የዘርፉን የፖሊሲ ማዕቀፍ ያስተዋወቀችበት፣ የአፍሪካና የአሜሪካ የቢዝነስ ትስስር ምን መምሰል እንዳለበት እይታዋን ያካፈለችባቸው መድረኮች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ትብብር መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሥምምነትም ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ የጀመረቻቸውን ሰፋፊ ጥረቶች ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን አብራርተዋል።

ሥምምነቱ ከሁለት መቶ ሚሊየን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ካፒታል የያዘ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ኢትዮጵያ የቱርዝም መሰረተ ልማት በማስፋፋትና መዳረሻ ቦታዎችን በማልማት ምቹ ለማድረግ የያዘችውን ውጥን የሚያግዝ መሆኑን አስረድተዋል።

በተጓዳኝም፤ በጉባኤው የተለያዩ የግንኙነት መረቦች መዘርጋታቸውንም አምባሳደሩ ጨምረው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ልዑክ በዚህ ጉባኤ ላይ መሳተፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በማሰናሰን ኢትዮጵያ ለቢዝነስ ዲፕሎማሲ የሰጠችውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑንም ገልጸዋል።

አምባሳደሩ አክለውም ጉባኤው የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጥረቶች ለማጠናከር ዕድል የፈጠረ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ጉባኤው በዋናነት ለኢትዮጵያ ምርቶች ገበያ በማፈላለግ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል በማስፋትና፣ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎችን በማፈላለግና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸዋል።

የዘንድሮው የአፍሪካ-አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ አሜሪካ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአስተዳደር ዘመን አፍሪካን በተመለከተ የምትከተለው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ድጋፍን መሰረት ካደረገው ወደ ቢዝነስ ዲፕሎማሲ እንዲሸጋገር የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ መካሄዱ ልዩ አድርጎታል።

ኢትዮጵያ 10ኛውን የአፍሪካ-አሜሪካ ጉባኤ ማዘጋጀቷ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026