አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ካላት ብዝሃ ህይወት ህዝቦቿን የምትጠቅምበት እና ድህነትን የምታሸንፍበት መንገድ ለማድረግ በትብብር መስራት እንደሚገባ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ገለፁ።
የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት እያከናወነ ያለውን ስራና ቀጣይ አቅጣጫ በተመለከተ ከክልል ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወትን ጨምሮ የበርካታ ሀብትና ፀጋ ባለቤት ነች።
ኢትዮጵያ ከ 6 ሺህ በላይ የእፅዋትና 7ሺህ በላይ የእንስሳት ዝርያ እንዳላትና ከዚህ ውስጥም 10 በመቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ያለንን ብዝሃ ህይወት ጠቀሜታን ማወቅና መጠበቅ እንዲሁም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባልም ብለዋል።
ብዝሃ ህይወት ለምግብና ለመድኃኒትነት እንዲሁም የተለያዩ ጥቅሞች ያሉት መሆኑን ገልፀው፤ ከሰው አኗኗርና ደህንነት ጋር የተያያዘ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በአየር ንብረት ለውጥና በተለያዩ ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ብዝሀ ህይወት የመመናመንና የመጥፋት አደጋ እንደሚጋረጥበት ተናግረዋል።
አረንጓዴ አሻራ፣ አፈር ጥበቃና ሌሎች ስራዎች ለብዝሀ ህይወት ጥበቃ አስተዋጽኦ እንዳላቸውም ገልጸዋል።
የብዝሀ ህይወት ለስራ እድል፣ ለማህበራዊና ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ጠቁመው፤ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የድርሻውን እንዲወጣ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ካላት ብዝሃ ህይወት ህዝቦቿን የምትጠቅምበትና ድህነትን የምታሸንፍበት መንገድ ለማድረግ በትብብር መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025