የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በኦሮሚያ ክልል በትራንስፖርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት እየተስፋፋ ይገኛል

Jun 27, 2025

IDOPRESS

አዳማ ፤ ሰኔ 19/2017( ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል በትራንስፖርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችንና ሌብነትን ለማስወገድ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት እየተስፋፋ እንደሚገኝ የክልሉ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ገለፀ።

በዘርፉ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በሚደረገው ንቅናቄ ሙያተኞችና አመራሮች የድርሻቸውን እንዲወጡ በስነ-ምግባር ግንባታ ላይ ያተኮረ መድረክ በአዳማ ተካሄዷል።


የኦሮሚያ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ምክትል ሃላፊ አቶ ለችሳ ሀዩ እንደገለፁት ኤጀንሲው በዘርፉ የሚስተዋል የሙስና፣ ብልሹ አሰራርና ሌብነትን ለማስወገድ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዲጂታል የአሰራር ስርዓት እየዘረጋ ነው።

በተለይ በዘርፉ የነበሩ የሌብነትና ብልሹ አሰራር ተጋላጭነትን ለመቀነስ የትራንስፖርት ስምሪት ዲጂታል በማድረግና አቅርቦቱን ለማሳለጥ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም በትራንስፖርት መናኸሪያዎች አገልግሎትን ዲጂታል ማድረግና የቁጥጥር ቴክኖሎጂን ማስፋፋት እንዲሁም አጠቃላይ አሰራር እንዲዘምን እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

አገልግሎቱን ከማዘመን ጎን ለጎን በስነ-ምግባር የታነጹ አስፈፃሚዎችና ፈፃሚዎችን ለማብዛት ከክልል ጀምሮ እስከ ታችኛው የአስተዳደር መዋቅር ድረስ ያሉ የትራንስፖርት ዘርፍ ሙያተኞችን የማነጽ ተግባርም እየተከናወነ ይገኛል ነው ያሉት።

በኤጀንሲው የትራፊክ ደህንነት ዳይሬክተር አቶ ሙስባሁዲን አብዱልመጅድ በበኩላቸው በዘርፉ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በተደረገ ጥረት 500 በየደረጃው ያሉ ሙያተኞች ላይ የተለያየ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

በተወሰደው እርምጃም ተጠያቂነት የሰፈነበት አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽ ለማድረግ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስረድተዋል።


በተለይ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ማዕከላት ስልጠናና የመንጃ ፍቃድ ፈተና 'ኦንላይን' እንዲሆን የተደረገ ሲሆን '8556' ነፃ የስልክ መስመር በመጠቀም ህብረተሰቡ የሚያጋጥሙትን ችግሮች እንዲያጋልጥ አሰራር መዘርጋቱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በትራንስፖርት መናኸሪያዎች ዲጂታል ቲኬት ላይ የአሽከርካሪው ሙሉ ስም፣ የተሽከርካሪ የሰሌዳ ቁጥርና ነፃ የስልክ መስመር ጭምር በማስገባት ሌብነትና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ስራ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026