የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በዞኑ በመኸሩ ወቅት ከ432 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያየ ሰብል ለማልማት የእርሻ ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል

Jun 27, 2025

IDOPRESS

ደሴ፤ ሰኔ 20/2017(ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በመኸሩ ወቅት የተሻሻሉ አሰራሮችን በመጠቀም ከ432 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያየ ሰብል ለማልማት የእርሻ ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ፡፡

የዘንድሮው የክረምት ዝናብ ለሰብል ልማት አመቺ በመሆኑ አርሶ አደሩ ምርታማነቱን ለማሳደግ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት ተመልክቷል።

የዞኑ ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ደመቀ አድማሱ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አርሶ አደሩ ምርታማነቱን በማሳደግ በምግብ ራሱን ከመቻል ባለፈ ምርት ለገበያ በስፋት ማቅረብ እንዲችሉ ተገቢው ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ነው።

በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከ432 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያየ ሰብል ለማልማት የእርሻ ሥራው በትራክተር በመታገዝ ጭምር ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።


እስካሁን ከታረሰው ውስጥም ከ18 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት ላይ ማሽላና በቆሎ መዘራቱን ጠቅሰዋል፡፡

የተለያዩ የተሻሻሉ አሰራሮችን በመጠቀም ከመኸር ልማቱ ከ15 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ጥቁር አፈርን በማጠንፈፍ፣ በመስመር በመዝራት፣ ማዳበሪያን በመጠቀም፣ በኩታ ገጠም በማልማትና አርሶ አደሩን በማንቃት ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አርሶ አደር ሰይድ ሙሄ በዞኑ ወረባቦ ወረዳ የ02 ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ፤ ሁለት ሄክታር መሬታቸውን በማሽላና ጤፍ ለማልማት ማሳቸውን አለስልሰው የዘር ሥራ መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

በግብርና ባለሙያዎች ድጋፍ ታግዘው ጠንከረው በመስራት የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ ጠቁመው፤ የሚፈልጉትን ግብዓትም በወቅቱ ማመቻቸታቸውን አመልክተዋል፡፡


በዘንድሮው የመኸር ወቅት የተሻሉ አሰራሮች ተጠቅመው ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እየሰራን ነው ያሉት ደግሞ በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የ07 ቀበሌ አርሶ አደር አደም አሊ ናቸው፡፡

በዚህም አንድ ሄክታር ተኩል ማሳቸውን በማሽላ፣ ቦለቄና ጤፍ ለማልማት ሥራቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የምስራቅ አማራ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል የትንብያና ቅደመ ማስጠንቀቂያ ዴስክ ኃላፊ ወይዘሮ ሉባባ መሀመድ በበኩላቸው ፤ ደቡብ ወሎን ጨምሮ ክረምቱ በምስራቅ አማራ ወቅቱን ጠብቆ ከመግባቱ ባለፈ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይጠበቃል ብለዋል፡፡


በተለይ ሀምሌና ነሀሴ ላይ ከፍተኛ ዝናብ እንደሚኖር ትንብያው እንደሚያሳይ ጠቁመው፤ ቅጽበታዊ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ሊያጋጥም ስለሚችል ህብረተሰቡ ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስበዋል፡፡

በክረምቱ የሚጥለውን መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም አርሶ አደሩ የሰብል ምርታማነቱን ሊያሳድግ እንደሚገባ ያመለከቱት ደግሞ የማዕከሉ የልማት ሚቲዎሮሎጂ ዴስክ ኃላፊ አቶ እንዳላማው ወልዴ ናቸው።

ዝናቡ ከፍተኛ ስለሚሆን በማሳ ላይ ውሃ እንዳይተኛ የውሃ መፋሰሻ ቦዮችን መስራት፤ ከዝናቡ ብዛት አንጻር አረም መብዛትም ስለሚኖር ሰብሉን በወቅቱ ማረም እንደሚገባም ጠቁመዋል።


ከዚህ ጎን ለጎንም የሚጥለውን ዝናብ በማሳ ዳር ዳር አቅቦ በማስቀረት ወደ ግድቦችና ኩሬዎች እያስገቡ ውሃ በማሰባሰብ ለበጋ መስኖ መጠቀም እንዲቻል ማመቻቸትም እንዲሁ፡፡

የክረምት ዝናቡ ለሰብል ልማት፣ ለእንሰሳት ግጦሽ፣ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማትም የሚያስገኘው ጠቀሜታ ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል።

በደቡብ ወሎ ዞን ባለፈው ዓመት በመኸሩ ወቅት ከለማው መሬት 13 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን ከግብርና መምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025