ሰበታ፤ ሰኔ 21/2017(ኢዜአ)፡- በሸገር ከተማ አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ የሚያሳድጉ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ።
በሸገር ከተማ አስተዳደር ፉሪ፣ ገላን ጉዳና ሰበታ ክፍለ ከተማዎች ከ11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የከተማው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የከተማውን ነዋሪ ህዝብ ተጠቃሚነት ይበልጥ የሚያሳድጉ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናክረው ቀጥለዋል።
ግንባታቸው የተጠናቀቁ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችም ለአገልግሎት ክፍት እየተደረጉ መሆኑን ገልጸው፤ ፕሮጀክቶቹ ከተማዋን የንግድ እና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የሚያግዙ ናቸው ብለዋል።
የነዋሪውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በማቃለል ተጠቃሚነቱን ይበልጥ የሚያረጋግጡ ናቸውም ብለዋል።
ዛሬ ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከልም የኮሪደር ልማት፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ለአቅመ ደካማዎች የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች፣ መንገዶችና ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።
እየተገባደደ ባለው በጀት ዓመት ሌሎችም የልማት ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውንም አውስተዋል።
የከተማው ህዝብም የልማት ፕሮጀክቶቹ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ መንከባከብ እና መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል።
የፉሪ፣ ገላን ጉዳና ሰበታ ክፍለ ከተማ አስተዳደሮች በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቶቹ በመንግስት በጀትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ መገንባታቸውን ገልጸዋል።
ፕሮጀክቶቹ በክፍለ ከተሞቹ አስተዳደሮች የሚስተዋሉ የመሰረተ ልማቶችን እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን የሚያግዙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቶቹ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከመፍታት በዘለለ በግንባታው ሂደት ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል የፈጠሩ እንደሆኑም አብራርተዋል።
ከከተማዋ ነዋሪዎችም ለአገልግሎት የበቁት የመሰረተ የልማት ፕሮጀክቶች የረጅም ጊዜ ጥያቄያቸውን የመለሱ መሆናቸውን በዚህም መደሰታቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025