
ሐረር፤ ሰኔ 23/2017 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ከለውጡ ዓመታት ወዲህ እየተገነቡ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያጎለበቱ መሆኑን የጨፌ ኦሮሚያ ምክትል አፈ ጉባዔ ኤልያስ ኡመታ አስታወቁ።
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች የተገቡትን የልማት ፕሮጀክቶች የመረቁት የጨፌ ኦሮሚያ ምክትል አፈ ጉባዔ ኤልያስ ኡመታ እንደተናገሩት በክልሉ ከለውጡ ዓመታት ወዲህ የልማት ፕሮጀክቶች በስፋት እየተገነቡ ነው።

በክልሉ በተለያዩ ዞኖች እየተገነቡ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና ፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት እየበቁ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ፕሮጀክቶቹም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያጎለበቱ መሆኑን ጠቅሰው በዚህም የአመራሩ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል።
በዞኑ ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ የተገነቡ 310 ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት መብቃታቸውን የተናገሩት ደግሞ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሚስኪ መሀመድ ናቸው።

ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸው በዞኑ ምርትና ምርታማነት ከማጎልበት ባለፈ በህዝቡ ዘንድ ሲነሳ የነበረውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ የሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ ከ2014 ዓም ጀምሮ የ73 የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት ስራ ተጀምሮ እስከ አሁን 33ቱን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን የተናገሩት ደግሞ የኦሮሚያ ክልል መስኖና አርብቶ አደር ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ አለሙ ረጋሳ ናቸው።
ግድቦቹ ከመስኖ ልማት በተጨማሪ ለእንስሳት መጠጥ ውሃ፣ ለአሳ እርባታ፣ ለኢኮ ቱሪዝምና ለሌሎች አገልግሎት በማዋል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።
በአካባቢያቸው ለእንስሳት መጠጥና ለመስኖ ልማት የሚሆን ውሀ ይቸግራቸው እንደነበር ያስታወሱት ደግሞ በዞኑ የጭናክሰን ወረዳ ነዋሪ ከፊል አርሶ አደር ኡስማኢል አህመድ ናቸው።

አሁን የተገነባው ግድብ ለነበረባቸው ችግር መፍትሄ የሰጠ መሆኑን ጠቁመው በተለይ ግድቡ ከመስኖ ልማት በተጨማሪ ለአሳ እርባታና ለሌሎች የልማት ስራዎች ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
በቀበሌያቸው የተገነቡ የውሃ ፕሮጀክቶች ለከብቶቻችውና ለእርሻ ስራቸው ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በጭናክሰን ወረዳ የመረር ቀበሌ ነዋሪ ከፊል አርሶ አደር ሁሴን ዮኒስ ናቸው።
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የተገነቡ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማት፣ ድልድዮች፣ የመስኖ ግድቦች፤ የአስተዳደር ህንጻዎችና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026