የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በክልሉ የህዝቡን የመልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተደረጉ ጥረቶች ውጤት አስመዝግበዋል

Jul 1, 2025

IDOPRESS

ወላይታ ሶዶ፤ሰኔ 23/2017 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህዝቡን የመልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተደረጉ ጥረቶች ውጤት አስመዝግበዋል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተናገሩ።

"ጠንካራ ክልላዊ አንድነትና አብሮነት ለዘላቂ ሠላምና ብልጽግና" በሚል መሪ ሃሳብ በወላይታ ሶዶ ከተማ ክልል አቀፍ የሠላም፣ የልማት እና የአንድነት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።


ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት፥ የክልሉን ህዝቡ የመልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ በተደረጉ ጥረቶች በኢኮኖሚው ፣ በማህበራዊና በፖለቲካው ዘርፎች ስኬቶች ተመዝግበዋል።

የልማት ስራዎቹ የህብረተሰቡ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያገናዘቡ እንዲሆኑ ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል።

የመንግስት ተቋማት ሽፋንና የአገልግሎት ተደራሽነትን በማሳደግ የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ለውጦች መታየታቸውን አንስተዋል።

የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ በበኩላቸው፥ ክልሉ ከተደራጀ ጊዜ አንስቶ የሕዝቡን ሁለንተናዊ ጥያቄዎች ለመመለስ በተሰራው ስራ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

የፖለቲካ እሳቤን በማዘመን የህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ዕሴትን በማስረጽ በኩልም ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን አብራርተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት አቶ ያዕቆብ አልታዬ በበኩላቸው፥ በክልሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል ተባብሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለዚህ ደግሞ የአመራር ቁርጠኝነትና የህዝቡ ትብብር አስፈላጊ በመሆኑ በቅንጅት መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል ።

''ጠንካራ ክልላዊ አንድነትና አብሮነት ለዘላቂ ሠላምና ብልጽግና" በሚል መሪ ሃሳብ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ያለው ክልል አቀፍ የሠላም፣ የልማት እና የአንድነት ኮንፈረንስ ነገም ቀጥሎ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026