
ጊምቢ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፡-በኦሮሚያ ክልል ከተሞች የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች የሚመልሱ የመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን በክልሉ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የከተማ ልማት አስተባባሪ አቶ መስፍን መላኩ ገለጹ።
በምዕራብ ወለጋ ዞን ዪብዶ ወረዳ ግንባታቸው የተጠናቀቁ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ተቋማት የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።

ተመርቀው ለአገልግሎት ከበቁ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች መካከል የወጣቶች ማዕከል፣ 'ዪብዶ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት እና ሌሎች ይገኙበታል።
በመሰረተ ልማት ተቋማቱ ምረቃ ላይ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የከተማ ልማት አስተባባሪ አቶ መስፍን መላኩ፣ በክልሉ ከተሞች የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታ በስፋት እየተካሄደ ነው።

የክልሉ መንግሥት ከለውጡ በኋላ የህዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ስራዎችን በትኩረት እያከናወነ መሆኑን ገልጸው የመሰረተ ልማት ተቋማት ደግሞ ስፊውን ድርሻ ይዘዋል ብለዋል።
በክልሉ ከተሞች በበጀት ዓመቱ ግንባታቸው ሲከናወን የቆዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ሰሞኑን ተመርቀው ለአገልግሎት እየበቁ እንደሚገኙም አመልክተዋል።
በቀጣይም በከተሞች የህዝቡን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታ ይጠናከራል ብለዋል።

በተለይም በምዕራብ ወለጋ ዞን ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቁ የመሰረተ ልማት ተቋማት የአካባቢውን ልማት የሚያነቃቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በዞኑ ተስፋ ሰጪ የልማት እንቅስቃሴ እየታየ መምጣቱን ጠቅሰው ህዝቡም ከየትኛውም ጊዜ በላይ የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የምዕራብ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ተረፈ በበኩላቸው በዞኑ ዘላቂ ሰላምን ከማጽናት ጎን ለጎን የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የአጭር እና የረጅም ጊዜ እቅድ ተዘጋጅቶ እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል።

በዛሬው እለትም ከ249 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የመሰረተ ልማት ተቋማት ለህዝብ አገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ገልጸዋል።
መንግስት የመልካም አስተዳደር ችግር መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን ለይቶ መፍትሄ ለመስጠት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስረድተዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026