🔇Unmute
ሀዋሳ፤ መስከረም 19/2018 (ኢዜአ)፡-በሲዳማ ክልል የቡና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለፀ።
በሲዳማ ክልል "የለማ ቡና ለቤተሰብ ብልፅግና " በሚል መሪ ሀሳብ ክልላዊ የቡና ልማት የንቅናቄ መድረክ ዛሬ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አስፋው ጎኔሶ በክልሉ የቡና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
በክልሉ ለቡና አመራረትና አሰባሰብ ሂደት ተገቢ ትኩረት በመስጠት ጥራት ያለው ቡና ለገበያ በማቅረብ የአምራች አርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስረድተዋል።
በዚህም ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ጠቅሰው በቀጣይም ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
ቡና ለሀገር የውጭ ምንዛሬ በማስገኘትና ክልሉንም በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት አስተዋጾ እያደረገ መሆኑ ተናግረዋል።
እንደአቶ አስፋው ገለጻ በአርሶ አደሩ የቡና ማሳ ላይ ከሚከናወኑ ሥራዎች በተጨማሪ ሕገወጥ የቡና ዝውውርን ለመቆጣጠር የተሰጠው ትኩረት በቡና ጥራት ላይ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው።
ይህንን ሥራ በተያዘው በጀት ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ኃላፊው፣ እስከ ቀበሌ ድረስ የተደራጁ ግብረ ኃይሎችን በማነቃነቅ ጠንካራ የቁጥጥር ሥራ ለመስራት ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በክልሉ በቡና የሚለማ 175 ሺህ ሄክታር መሬት መኖሩን ጠቅሰው፣ በልማቱም ከ400 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ለቡና ጥራትና ምርታማነት በትኩረት መስራት የአምራች አርሶ አደሮችን ሕይወት ማሻሻል እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡
አቶ መምሩ እንደገለጹት አርሶ አደሩ የቡና ማሳውን በአግባቡ እንዲይዝ፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ እንዲጠቅም እንዲሁም ያረጁትን የቡና ዛፎችን በጉንደላ በማደስና ሌሎች የምርታማነት ማሳደጊያ ፓኬጆችን በመተግበር ምርታማነትና ገቢውን ለማሳደግ እየተሰራ ነው።
በዚህም የቡና ምርትና ምርታማነት እያደገ ከመምጣቱ ባለፈ በማሳ ሽፋን ላይ እየታየ ያለውን አድገት ለማስፋት ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ቃሬ በበኩላቸው ባለፉት ዓምስት ዓመታት በክልሉ የቡና ልማት ላይ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በነዚህ ዓመታት የቡና ማሳ ሽፋንን ከ153 ሺህ ሄክታር ወደ 175 ሺህ ሄክታር ማደጉንና ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርብ የቡና መጠንም ከ25 ሺህ ቶን ወደ 40 ሺህ ቶን ለማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል።፡
ከዚህ በፊት በክልሉ በሄክታር የሚገኘው ቡና ከስምንት ኩንታል ያልዘለለ እንደነበር አቶ መስፍን አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ከሄክታር 11 ኩንታል የቡና ምርት ማግኘት እንደተቻለ ጠቅሰዋል፡፡
በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ ምርታማነትን በሄክታር ወደ 15 ኩንታል ከፍ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ ነው ሲሉም አክለዋል።፡
በንቅናቄ መድረኩ ላይ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
አሶሳ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ የህብረት ስራ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክ...
Apr 29, 2026
ባህርዳር ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ የገቢ አሰባሰብ ስርአትን በመተግበር ረገድ የተገኘው ውጤት ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት...
Apr 15, 2026
ሮቤ፣ ሚያዝያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎችን ለተሻለ ውጤት ማብቃት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወ...
Apr 14, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025