የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

‎በሲዳማ ክልል በበጀት ዓመቱ ከ40 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ይቀርባል

Oct 11, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

‎ሀዋሳ ፤ መስከረም 30/2018 (ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል በበጀት ዓመቱ ከ40 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ እንደሚቀርብ የክልሉ ቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ገለፀ ።

ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ቃሬ እንደገለፁት በተያዘው በጀት ዓመት 40 ሺህ 169 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከዚህ ውስጥ 85 በመቶ የሚሆነው የታጠበ ቡና ሲሆን ቀሪው ያልታጠበ እንደሚሆን አቶ መስፍን ገልፀው እቅዱንም ለማሳካት የታጠበ ቡና ከሚያዘጋጁ 425 ኢንዱስትሪዎች መካከል 70 በመቶዎቹ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል ፡፡


ኢንዱስትሪዎቹ ጥራት ያለው ቡናን እንዲያመርቱም የግንዛቤ፣ የድጋፍና ክትትል ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመዋል፡፡

ቡናን ከአርሶ አደሩ በሚረከቡበት ወቅት እሸቱን ብቻ በመቀበል የጥራት ደረጃውን ማስጠበቅ ላይ እንዲያተኩሩ መሰራቱን አስረድተዋል፡፡

የቡና ግብይቱን ጤናማነት ለማረጋገጥ ህገወጥ የምርት ዝውውርን ለመቆጣጠር እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ የጋራ ግብረ ኃይል መዋቀሩን ገልፀዋል፡፡

በክልሉ ከ401 ሺህ በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች በቡና ምርት ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን ጠቅሰው አርሶ አደሩ ለኢንዱስትሪው የሚያቀርበው ቡና ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡

የቡና ግብይትን ጤናማ ለማድረግ ከሚሰራው ስራ ጎን ለጎንም ምርታማነቱን ለማሳደግ ለአርሶ አደሩ የተሻሻሉ ዝርያዎች መቅረባቸውንና የባለሙያ ድጋፍ መደረጉን አክለዋል።

አርሶ አደሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያ አጠቃቀምና ሌሎች የፓኬጅ ሥራዎችን ማሻሻል በመቻሉ በሄክታር የሚገኘው የምርት መጠንም እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡


ለአብነትም ከዚህ በፊት በሄክታር የሚገኘው ቡና ከሰባት ኩንታል ያልበለጠ እንደነበር ጠቅሰው ባለፈው አመት 11 ነጥብ 04 ኩንታል በሄክታር ምርት ማግኘት እንደተቻለ አስረድተዋል፡፡

የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቶን የተፈጥሮ ማዳበሪያ ጥቅም ላይ መዋሉን ተናግረዋል ፡፡

የቡና ምርት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን ለማጉላት ጥራቱን የጠበቀ አመራረት፣ አሰባሰብና ግብይት እንዲኖር ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በቁርጠኝነት እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የቡና ምርት ብዛትና ጥራትን ለማስጠበቅ ባለፉት አምስት ዓመታት ክልሉ ባከናወነው ተግባርም ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርበውን የቡና መጠን ከ25 ሺህ ቶን ወደ 40 ሺህ ቶን ማሳደግ መቻሉን ከባለሥልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል-ሰልጣኞች

አሶሳ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ የህብረት ስራ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክ...

Apr 29, 2026

በአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በመተግበር ረገድ የተገኘው ውጤት ልምድ የሚወሰድበት ነው

ባህርዳር ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ የገቢ አሰባሰብ ስርአትን በመተግበር ረገድ የተገኘው ውጤት ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት...

Apr 15, 2026

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ነው

ሮቤ፣ ሚያዝያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎችን ለተሻለ ውጤት ማብቃት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወ...

Apr 14, 2026

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025