🔇Unmute
ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 4/2018(ኢዜአ)፦ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተሻሻለ የእንስሳት መኖን ለአካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰራ አስታወቀ።
ዩኒቨርሲቲው በ45 ሚሊዮን ብር ወጭ ያስገነባው የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ዛሬ ተመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስማረ መለስ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን የአካባቢውን ጸጋ መሰረት በማድረግ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች እያከናወነ ይገኛል።
በተለይ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ለዚህም ዩኒቨርሲቲው የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በማርባት በወተት አቅርቦት ራሱን ከመቻል ባለፈ የአካባቢው አርሶ አደሮች ሳይንሳዊ የእንስሳት እርባታ ላይ እንዲያተኩሩ እያከናወናቸው ያሉ ተግበራትን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
በአካባቢው በእንስሳት ርባታና ማድለብ ሥራ ምርታማነት ለማሳደግም በ45 ሚሊዮን ብር ወጭ ያስገነባውን የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ዛሬ ማስመረቁንም አስማረ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

እንደእሳቸው ገለጻ ፋብሪካው በሰዓት ከ50 ኩንታል በላይ የመኖ ምርት በማምረት የወተትና የሥጋ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ነው።
በዚህም ዩኒቨርሲቲው የተሻሻለ የእንስሳት መኖን ለአካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ አርሶ አደሩን በዘላቂነት ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመራቸውን ሥራዎች ያጠናክራል ብለዋል።
በቀጣይም የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ማቀዱን ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅትም ዩኒቨርሲቲው ባለ ሰባት እና ባለ ስድስት ወለል የመምህራን መኖሪያ ቤት ሕንጻዎችን እያስገነባ እንደሚገኝ የተናገሩት አስማረ (ዶ/ር) ፣ ሕንጻዎቹ ከመምህራን መኖሪያ ቤት በተጨማሪ ለንግድ፣ ለመዝናኛና የጋራ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ከፍሎችን አካተው እየተገነቡ መሆኑን አስረድተዋል።

የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባል ወይዘሮ መሰንበት ሸንቁጤ በበኩላቸው እንዳሉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ወደ ራስ ገዝነት በመሸጋገር ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል ማምረት እንዳለባቸው አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ ነው።

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ እየተገበራቸው ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የራሱን አቅም በማሳደግ በቀጣይ ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር የሚያስችሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ዛሬ የተመረቀው የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካም የአካባቢውን የእንስሳት እርባታ ሥራ በመደገፍ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ ዩኒቨርሲቲው እያስገነባው ያለው የመምህራን መኖሪያ ቤት ሕንጻ በመምህራን ሲነሳ የነበረውን ችግር ለመፍታት ያስችላል ብለዋል።
በቀጣይ ከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን እድገት ለማፋጠን ከዩኒቨርሲቲው ጋር በትብብር እንደሚሰራ አመልክተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025