🔇Unmute
ቦንጋ፣ ጥቅምት 6/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡናን በብዛትና በጥራት በማምረት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን አስታወቀ።
የክልሉ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ለተለያዩ የዘርፉ ባለሙያዎችና የሚመለከታቸው አካላት የቡና አዘገጃጀትና ጥራት ማስጠበቅ ላይ ያተኮረ ስልጠና እየሰጠ ነው።

በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር የደረጉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አስራት መኩሪያ፤ በክልሉ ከቡና ልማትና ምርታማነት በተጨማሪ ለጥራት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።
የቡና ምርትና ጥራት የሚረጋገጠው በሁሉም ጥረትና ትብብር ቢሆንም በተለይም የባለሙያዎች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህም መሰረት የቡና ምርት ዝግጅትና ግብይት ሂደት የተሳለጠ እና ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን የባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻዎችን ግንዛቤ የማሳደግ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
በክልሉ ቡናን በብዛትና በጥራት በማምረት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አረጋግጠዋል።
በመሆኑም የቡና አምራቾችና የመፈልፈያ ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና አርሶ አደሮች ለቡና ምርት ጥራት ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026