🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአባልነት ድርድሩን በካሜሩን ያውንዴ በፈረንጆቹ መጋቢት 2026 በሚካሄደው የዓለም የንግድ ድርጅት 14ኛ የሚኒስትሮች ጉባዔ ወቅት ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ መሆኗን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ገለጹ።
ገዥው ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) በዓለም የንግድ ድርጅትና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች የአሜሪካ ረዳት የንግድ ተወካይ ኒል ቤክ ጋር የኢትዮጵያን የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ድርድርን በተመለከተ ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የኢትዮጵያን የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት አስመልክቶ የተካሄደውን የስድስተኛ የስራ ቡድን ስብሰባ ውጤት እና ከስብሰባው በኋላ የተከናወኑ ቁልፍ ማሻሻያዎችን አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ የአባልነት ድርድሩን በካሜሩን ያውንዴ በፈረንጆቹ መጋቢት 2026 በሚካሄደው የዓለም የንግድ ድርጅት 14ኛ የሚኒስትሮች ጉባዔ ወቅት ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ መሆኗን ነው የገለጹት።
የአባልነት ሂደቱ በተቀመጠ የጊዜ ገደብ እና በተጨባጭ ስራ፣ በትጋት እና የንግድን መዋቅራዊ ለውጥ የማምጣት አቅምን በሚገነዘብ አመራር መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ድርጅቱን ለመቀላቀል አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን ለማሟላት ያላትንም ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ከአባል ሀገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የምታገኘውን ከፍተኛ ድጋፍ ጠቅሰው፤ አሜሪካም በዚህ ረገድ የተጠናከረ ድጋፍ እንድታደርግ ነው የጠየቁት።
በዓለም የንግድ ድርጅት እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች የአሜሪካ ረዳት የንግድ ተወካይ ኒል ቤክ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እየሰራችው ያለውን ስራ አድንቀው አሜሪካ ተገቢውን ተሳትፎ እንደምታደርግ አስታውቀዋል።
የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ማሟላት ያለባትን መስፈርት በግልፀኝነት ለማሳወቅም እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026