የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የጌዴኦ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ የዞኑን የልማት አቅሞችና ባህላዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅ ተጨማሪ አቅም ነው   

Oct 29, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ዲላ፤ ጥቅምት 17/2018 (ኢዜአ)፡-የጌዴኦ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ የዞኑን የልማት አቅሞችና ባህላዊ እሴቶች ለማስተዋወቅ ተጨማሪ አቅም መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።

የጌዴኦ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ መደበኛ ስርጭቱን ዛሬ በይፋ ጀምሯል።

በወቅቱ ‎የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) እንደገለጹት የጌዴኦ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ የጌዴኦን የልማት አቅሞች ባህላዊ እሴቶችና የቱሪዝም ሀብቶች ለማስተዋወቅና አብሮነትን ለማጠናከር የጎላ ሚና አለው።


የጌዴኦ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ መደበኛ ስርጭት መጀመሩ በዚህ ረገድ የራሱ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው፣ በተለይ የጌዴኦን ባህላዊ እሴቶችና የቱሪዝም ሃብቶች በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ድርሻቸው የጎላ ነው ብለዋል።

ጣቢያው የህዝቦችን ትስስር ከማጠናከር ባለፈ ሀገራዊና አካባቢያዊ ልማቶችን ለማፋጠንና የመረጃ ፍሰትን ለማሳለጥ ጠንክሮ መስራት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የማህበረሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱና የጋራ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የጌዴኦ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላለፉት ዘጠኝ ወራት በሙከራ ደረጃ ቆይቶ ዛሬ መደበኛ ስርጭት መጀመሩን የገለጹት ደግሞ የጣቢያው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ በቀለ ናቸው።

የህዝብን ባህልና ቋንቋ፣ የቱሪዝም ሀብቶች እንዲሁም የልማት ውጥኖችን በማስተዋወቅ የህብረተሰቡን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ጣቢያው ጌዴኡፋንን ጨምሮ በሦስት ቋንቋዎችና በተለያዩ ይዘቶች የ24:00 ሰዓት ስርጭት እንደሚኖረውም ገልጸዋል።

‎የጌዴኦ ቴሌቪዥን ጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ ፀጋዬ ኦብሴ በበኩላቸው ጣቢያው የህዝቦችን ትስስር በማጠናከርና ገዥ ትርክትን በመገንባት ረገድ ትልቅ ሥራ ይጠበቅበታል ብለዋል።

በተለይ የሰላም እሴቶችን በማጉላትና በህብረተሰቡ ውስጥ በማስረጽ ለህዝቦች አንድነትና የጋራ ተጠቃሚነት መትጋት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ለቴሌቪዥን ጣቢያው መቋቋም አስተዋጾ ላበረከቱ አካላት እውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025