🔇Unmute
ባሕርዳር፤ ጥቅምት 20 /2018 (ኢዜአ) ፡- በአማራ ክልል የተከሰተው የግሪሳ ወፍ በደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭትና በባሕላዊ ዘዴ የመከላከል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
በቢሮው የዕፅዋት ጥበቃ ባለሙያ አቶ አበበ አናጋው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ ሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርና ደቡብ ወሎ ዞኖች የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ ለመቆጣጠር በባህላዊና በአውሮፕላን የታገዘ ጥረት እየተደረገ ነው።
የግሪሳ ወፉ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት እየተከናወነ የሚገኘውም በተለዩ 22 የግሬሳ ወፍ የማደሪያ ቦታዎች ላይ መሆኑን አስረድተዋል።
ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባባር እየተከናወነ በሚገኘው የኬሚካል ርጭት ሥራም ከ100 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የለማ የማሽላና ሌሎች ሰብሎችን ከጉዳት መታደግ መቻሉን አንስተዋል።
ለርጭት የሚያገለግለው አውሮፕላን መነሻውን በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ በማድረግ ስራውን በውጤታማነት እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመው ፤ ለርጭት በማይመቹ ቦታዎች ደግሞ አርሶ አደሩ በባሕላዊ ዘዴ እንዲከላከል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የግሪሳ ወፍ ከማደሪያ ቦታው እስከ 64 ኪሎ ሜትር በመብረር የደረሰ ሰብልን የሚያጠፋ መሆኑን ጠቁመው፤ የተጀመረውን የመከላከል ስራ በማጠናከር ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማትና ጥበቃ ቡድን መሪ ደጀኔ ከበደ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ በዞኑ ዳዋጨፋና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳዎች በተለዩ አምስት የማደሪያ ቦታዎች የተከሰተውን የግሬሳ ወፍ የማጥፋት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
እስካሁን በተደረገው የኬሚካል ርጭት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የግሪሳ ወፍ በሚያድርበት ቦታ ማጥፋት መቻሉንና ቀሪውንም በአጭር ጊዜ ለማስወገድ እየተሰራ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025