የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በሐረሪ ክልል በዘንድሮ ዓመት በበጋ መስኖ 4 ሺህ 851 ሄክታር መሬት ይለማል

Nov 3, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ሐረር ፤ጥቅምት 23/2018(ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል በዘንድሮ የበጋ መስኖ 4 ሺህ 851 ሄክታር መሬት እንደሚለማ የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ነስረዲን አህመድ ለኢዜአ እንዳሉት በክልሉ በዘንድሮ የበጋ ወቅት መስኖ እርሻ ያሉትን የውሃ አማራጮች በሙሉ በመጠቀም 4 ሺህ 851 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡

በመስኖው የሚለማውም ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመን፣ ቃሪያ፣ ካሮትና ሌሎች የአትክልትና የሰብል ዓይነት መሆናቸውን ተናግረዋል።


በሁለት ዙር በመስኖ ከሚለማው መሬትም በድምሩ ከ1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ዘንድሮ በመስኖ የሚለማው መሬት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር በ402 ሄክታር መሬት ብልጫ እንዳለውም አቶ ነስሩ ተናግረዋል።

ለመስኖ ልማቱ ምርጥ ዘርና ሌሎች የምርት ማሳደጊያ ግብዓት በቢሮውና በወረዳዎች መሟላቱን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለመስኖ ልማቱ የሚያገለግል ተጨማሪ 200 የውሃ መሳቢያ ሞተሮችና ዲናሞ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱንም ተናግረዋል።


በየደረጃው ለሚገኙ የግብርና ባለሙያዎችና የልማት ጣቢያ ሰራተኞች አስፈላጊው የቴክኒክና የሙያ ስልጠና መሰጠቱንም ገልጸዋል።

በክልሉ ባለፈው ተመሳሳይ ዓመት 4ሺህ 449 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ መልማቱን ጠቅሰዋል።

የመስኖ ልማቱ በተለይም የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት አርሶ አደሩንና የከተማ ነዋሪውን በቀጥታ በማገናኘት የገበያ መረጋጋት እየፈጠረ እንደሚገኝና ህብረተሰቡም ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻሉም አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026