የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ የንግድ ሚዛንን በማስጠበቅ የተጀመረውን ፈጣን እድገት ለማስቀጠል ከመሻት ነው-ምሁራን

Nov 3, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ጋምቤላ፤ጥቅምት 23/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ የአገሪቷን የንግድ ሚዛን በማስጠበቅ የተጀመረውን ፈጣን እድገት ለማስቀጠል ከመሻት መሆኑን የጋምቤላ ዪኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ።

ኢትዮጵያ ከባህር በቅርብ ርቀት ላይ እያለች ወደ ባህር መግቢያ ተነፍጋ ለዓመታት የተቆለፈባት ሀገር ሆና ቆይታለች።

በዚህም ምክንያት ብዙ ዋጋ እየከፈለችና የሀገሪቷና የህዝቧ ህልውና አደጋ ላይ የወደቀ መሆኑ በተደጋጋሚ እየተነሳ ይገኛል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት የባህር በር የህልውና ጉዳይ መሆኑን በጽኑ በማመንና ጠንካራ አቋም በመያዝ በዲፕሎማሲው ረገድ በስፋት እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን እንዳሉት፥ የባህር በር ጥያቄ ለሀገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መሰረት የሚጥልና ህልውናን የማስቀጠል ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

በዩኒቨርሲቲው የምጣኔ ሃብት ትምህርት ክፍል መምህር ዘገዬ ሙሉ (ዶ/ር) እንዳሉት፥ የኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት የወጪና ገቢ ንግድ ሚዛን ላይ ከፍተኛ ጫና በማሳደር በሀገር እድገት ላይ ተጽኖ መፍጠሩን አስረድተዋል።


ይህን ጉዳይ ለመፍታትና ለሀገሪቱ ንግድ ሚዛን መጠበቅ መንግስት የጀመራቸው ጥረቶች ከውጤት እንዲደርሱ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን የመልማት ጥያቄም ሆነ የቀጣዩን ትውልድ ህልውና ለማስቀጠል የባህር በር ጥያቄ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በር እጦት የህዝብ ቁጭት ሆኖ መቆየቱን ያነሱት ደግሞ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ዓለም አቀፍ አጋርነት ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ጌታቸው በቀለ (ዶ/ር) ናቸው።


የባህር በር ጥያቄዋም የታሪክ ሆነ ህጋዊ መሰረት ያለውና የህልውና ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ያለመችውን እድገት ለማረጋገጥ የባህር በር ጥቅሙ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አንስተው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት አማካሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ጀምበሩ ዓለሙ(ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የታሪክ መዛግብት እንደሚያስረዳው አሰብ የኢትዮጵያ ወደብ እንደሆነ ነው ብለዋል።


ይሁን እንጂ ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ የባህር ወደብ አልባ ሆና መቆየቷ ታሪካዊ ስህተት ነው ያሉት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ፤የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢና ወቅታዊ መሆኑን ተናግረዋል።

ለኢትዮጵያ መልማት መሰረት የሆነውን የባህር በር የማግኘት መብትን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ማጠናከር ተገቢ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026