🔇Unmute
ደብረ ማርቆስ ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፡ - በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሶሰት ወራት ከሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ሃላፊ ተመስገን ተድላ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የከተማ አስተዳደሩ ለባለሃብቱ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት ከታቀደው ውስጥ በመጀመሪያዎቹ ሶሰት ወራት ከሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር በላይ ላስመዘገቡ 33 ባለሃብቶች ፈቃድ መሰጠቱን አስታውቀዋል።
ባለሀብቶቹ ለመሰማራት ፈቃድ ከወሰዱባቸው ዘርፎች መካከል የዘይት፣ ሚስማር ፣የጨርቃጨርቅና ዱቄት ፋብሪካ እንዲሁም ሆቴል እና ቱሪዝም እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።
ፈቃድ ከተሰጣቸው ውስጥ ለ20ዎቹ ባለሃብቶች ከ12 ሄክታር በላይ መሬት የተሰጣቸው ሲሆን፤ ቀሪዎቹንም ባቀረቡት ፕሮጀክት መሰረት ለማስተናገድ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በቀጣይም ተጨማሪ አዳዲስ ባለሃብቶችን በመሳብና ፈቃድ ለወሰዱት ደግሞ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ፈጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ የመደገፍ ተግባር እንደሚከናወን ተናግረዋል።
ፈቃድ የተሰጣቸው ባለሃብቶች ወደ ስራ ሲገቡም ከ3 ሺህ 600 በላይ ለሚሆኑ ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል መፍጠር የሚችሉ ናቸው ብለዋል።
ፈቃድ የወሰዱ ባለሃብቶች ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ28 ባለሃብቶችና በካፒታል ደግሞ ከአንድ ነጥብ ስምንት ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ተመልክቷል።
ብልጫ ያለው ውጤት ማስመዝገብ የተቻለው ከቀድሞ በተሻለ በከተማውና አካባቢ በተፈጠር ምቹ ሁኔታ ብዛት ያላቸው ባለሀብቶችን ባሉ የኢንቨሰትመነት አማራጮች ለመሳተፍ በማሰባቸው እንደሆነ አስረድተዋል።
በሌላ በኩል የኢንቨስትመንት ቦታ ለረጅም ጊዜ አጥረው ያስቀመጡ 52 ባለሃብቶችን ውል በማቋረጥ መሬቱን ለሚያለሙ ባለሃብቶች መመቻቸቱን ተናግረዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የኢንዱስትሪ ፓርክ ከሚገኙት 168 ፋብሪካዎች ውስጥ 36ቱ ወደ ማምረት የተሸጋገሩ መሆናቸው ተመልክቷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025