የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የደብረ ብርሃን ከተማ የህዝብ ቁርጠኝነትና የኢንዱስትሪ ጥንካሬ የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬነት ብሩህ ማሳያ ናቸው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Nov 13, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2018(ኢዜአ)፦ የደብረ ብርሃን ከተማ የህዝብ ቁርጠኝነትና የኢንዱስትሪ ጥንካሬ የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬነት ብሩህ ማሳያ መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባውን የብራውን ፉድ የብቅልና አልሚ ምግብ ማምረቻ ፋብሪካ መርቀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ደብረ ብርሃን በፈጠራ፣ በኢንተርፕራይዝና በኢንዱስትሪ ልማት ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች።

የደብረ ብርሃን ከተማ የህዝብ ቁርጠኝነትና የኢንዱስትሪ ጥንካሬ የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬነት ብሩህ ማሳያ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።

በመደመር መንግሥት ግልጽ ግብና ዕይታ መሰረት ሥራ በመፍጠርና ዕድልን በማስፋት የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ኢኮኖሚ እየተገነባ መሆኑን አንስተዋል።

የደብረ ብርሃን የኢንዱስትሪ ማዕከልነት የአማራ ክልልን የምርታማነት የራስ መተማመን አቅም በመገንባት ፋብሪካን ከማቆም የተሻገረ የአዲስ ዘመን ህያው መሰረት እንደሆነም አስረድተዋል።

የአማራ ክልል በለም አፈር፣ ታታሪና ስራ ወዳድ ህዝብ እንዲሁም ጥበበኛ እጆች የታገዘ የመልማት ከፍተኛ አቅም እንዳለው አብራርተዋል።


በቀጣይም ክልሉ የታደለውን ዕምቅ የልማት ጸጋ በአርሶ አደሮች፣ በሠራተኞች፣ በሥራ ፈጣሪዎችና በአመራሩ የተባበረ ክንድ ወደ እሴት መለወጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

መንግስትም የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያሳልጡ የመንገድና የኃይል አቅርቦት መሠረተ ልማቶችን የፖሊሲ እርምጃዎችን በመውሰድ የአልሚ ባለሃብቶችን የኢንቨስትመንት ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ ምህዳር እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የደብረ ብርሃን አካባቢ ጸጋዎች የወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነትና የኢንቨስትመንት ፍሰት በማሳደግ የምርታማነት ክብርን እንደሚያጎናጽፉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለዋል።

ከተማዋ የክልሉና የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ መነቃቃት ከሚያሳዩት አንዷ እንድትሆን አስችሏታልም ነው ያሉት።

በቀጣይም ኢንቨስትመንትና ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ስኬትን በማስፋት ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ደብረ ብርሃንን ሞዴል ከተማ የማድረግ ሥራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።

የተመዘገቡ ድሎችን በማስቀጠል ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ሩጫ መገንባት፣ ማሰልጠን፣ መፍጠርና ማስመረቅ መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

ከተማ የምርታማነት የክልል ዕድገትን በማሳለጥ የተረጋጋ የሥራ ባህልና ዘላቂ ስልጣኔ መሰረት በማስቀመጥ ጉልህ ሚና እንዳለውም አስረድተዋል።

በቀጣይም የባንዳና የባዕዳንን ዕኩይ ተልዕኮ በጽኑ በመታገል ለሀገር ዕድገትና ብልጽግና መሰረት የሚጥሉ የልማት ስራዎችን ማስፋት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025