🔇Unmute
ደሴ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ያለውን የተፈጥሮ ጸጋ እና ሀብት አልምቶ በመጠቀም ምርታማነትን የማላቅ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ።
ቢሮው ከክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር "ዘመናዊ ግብርና ለሁለንተናዊ ልዕልና" በሚል መሪ ሐሳብ የምክክር መድረክ በደሴ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የክልሉ ግብርና ቢሮ ደረጀ ማንደፍሮ እንደገለጹት፤ ክልሉ ለሰብል ልማት፣ ለእንስሳት እርባታና ለሌሎችም የግብርና ሥራዎች ምቹና ተስማሚ ነው።
ይህን የተፈጥሮ ጸጋና ሀብት አልምቶ ለመጠቀም የአሻጋሪ ዕድገትና የዘላቂ ልማት ፍኖተ ካርታ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል።

ፍኖተ ካርታውን ወደ መሬት በማውረድ የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ ለዘርፉ አመራር፣ ባለሙያና ባለድርሻ አካላት በየደረጃው ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
የምክክር መድረኩም የጋራ አመለካከትና ተልዕኮ በመያዝ በሁሉም አካባቢዎች የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
በዚህም በሰብል ልማት፣ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ በእንስሳት እርባታ፣ በሌማት ትሩፋትና በሌሎችም የተገኘውን አበረታች ውጤት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
እስካሁን የተመዘገበውን ውጤት በመገምገም ክፍተቶችን ለማረም፣ ዘመናዊ የግብርና ሽግግሩን ለማፋጠን፣ የመስኖ ልማትን ለማጠናከርና ተቋማዊና ሙያዊ ኃላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት የምክክር መድረኩ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
አርሶ አደሩን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለገበያ የሚተርፍ ምርት እንዲያመርት የሚያግዝ መሆኑን አስረድተዋል።
አርሶ አደሩ ከኋላ ቀር አሠራር ወደ ዘመናዊ ግብርና መሸጋገር እንዲችል ተገቢው ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑንም አክለዋል።
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ከክልል ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የዘርፉ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026