የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በክልሉ የአርሶ አደሮችን ገቢ ለሚያሳድጉና ለወጪ ንግድ የሚውሉ ምርቶችን በስፋት ለማምረት ትኩረት ተደርጓል

Jul 7, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የአርሶ አደሮችን ገቢ ለሚያሳድጉና ለወጪ ንግድ የሚውሉ ምርቶችን በስፋት የማምረት ስራ ትኩረት ማግኘቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ ገለጹ።

በክልሉ ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ ቦሎቄን በኩታ ገጠም የመዝራት ሥራ የክልሉ፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ተጀምሯል።


በዚሁ ወቅት የቢሮ ኃላፊው ኃይሉ አዱኛ በክልሉ የግብርና ምርታማነትን በእጥፍ ከመጨመር ጎን ለጎን፣ የአርሶ አደሮችን ገቢ ለማሳደግ በወጪ ንግድ ምርቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ዛሬ በዞኑ ቦሰት ወረዳ የዶንጎሬ ጪዮስ ቀበሌ የተጀመረው ቦሎቄን በኩታ ገጠም የመዝራት ሥራ ለዚህ አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው መሰል መልካም ተሞክሮዎች እንዲሰፉ ይደረጋል ነው ያሉት።

በተለይም የክልሉ አርሶ አደሮች ከግብርና ሥራ የሚያገኙትን ገቢ የበለጠ የሚያሳድጉ የቅባት እህሎችን በኩታ ገጠም እንዲያለሙ በትኩረት እንደሚሠራም አስረድተዋል።


የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አባቡ ዋቆ በበኩላቸው፣ በዞኑ ባለፈው ዓመት 90 ሺህ ሄክታር ገደማ መሬት ላይ የቅባት እህሎች መዘራታቸውን አስታውሰው፣ ዘንድሮ ይህንን ወደ 130 ሺህ ሄክታር ለማሳደግ መታቀዱን ተናግረዋል።

የተጀመረውን ሥራ የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም የግብርና ግብዓቶች በወቅቱ ለአርሶ አደሩ እንዲደርሱ መደረጉን ገልጸዋል።


በቦሰት ወረዳ ለመኸር እርሻ ከተዘጋጀው 64 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ 58 ሺህ ሄክታሩ በኩታ ገጠም የሚለማ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የወረዳው አስተዳዳሪ ጉተማ ቢፍቱ ናቸው።

በወረዳው በኩታ ገጠም ከሚለማው የቦሎቄ ሰብልም በሄክታር እስከ 30 ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026