የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመር፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ለተያያዙ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ የሚያስገኝ ነው

Jul 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጅማ ፤ሐምሌ 1/2018(ኢዜአ)፡- የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመር፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ለተያያዙ ችግሮቻችን ዘላቂ መፍትሄ የሚያስገኝ ነው ሲሉ የጅማ ዞን ማና ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ።

በጅማ ዞን ማና ወረዳ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች የዞኑና የወረዳው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ።


የማና ወረዳ ነዋሪዎች መንግሥት ለማኅበረሰቡ ጥያቄዎች ቅድሚያ በመስጠት እንደ መሶብ ያሉ ማዕከላትን ወደ ሥራ ማስገባቱ የገባውን ቃል በተግባር እየፈጸመ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በኢንቨስትመንት ሥራ ላይ የተሰማሩት የወረዳው ነዋሪ አቶ ዛኪር አወል በሰጡት አስተያየት፤ ከዚህ ቀደም ለአንድ ጉዳይ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ለማግኘት ብዙ ጊዜ ይባክንባቸው እንደነበር አስታውሰዋል።

ዛሬ አገልግሎት የጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ይህንን እንግልት እንደሚያስቀርላቸው ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።


ሌላኛው ነዋሪ አቶ መሐመድኑር ሸምሱ በበኩላቸው፣ ለዘመናት ይመኙት የነበረውን ፈጣን አገልግሎት በማዕከሉ ማግኘት መጀመራቸውን ጠቅሰው፣ አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ የተቀላጠፈ እንዲሁም ጊዜና ገንዘብን የሚቆጥብ በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ የማዕከሉ ስራ መጀመር ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ችግሮቻቸው ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያገኙ ተስፋ እንዲሰንቁ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።


የማና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሰመሩዲን አህመድ በበኩላቸው፣ በወረዳው በበጀት ዓመቱ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 32 ፕሮጀክቶች ተገንብተው መጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል።

ከተገነቡት መሠረተ ልማቶች መካከል ሁለት ድልድዮች፣ የወጣቶች መሥሪያ ሼዶች፣ የአስተዳደር ሕንጻ እንዲሁም የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።

በማዕከሉ 88 ዓይነት አገልግሎቶች በ9 መስኮቶች እንደሚሰጡ የገለጹት አስተዳዳሪው፣ በወረዳው ከሚገኙ 14 ሴክተሮች ውስጥ 10 የሚሆኑት ወደ ማዕከሉ እንዲገቡ መደረጉ የተገልጋዩን እርካታ ከፍ እንዳደረገው አብራርተዋል።

በዛሬው ዕለት በወረዳው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የ362 አቅመ ደካሞች ቤቶች ግንባታና እድሳት መጀመሩን አንስተዋል።


የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር፣ በዞኑ በማኅበረሰቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን የሚመልሱ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለነዋሪዎች ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ፣ የመንግሥትንና የዜጎችን ከአላስፈላጊ ወጪ መታደጉን ጠቁመዋል።

የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ቀላልና ዲጂታላይዝ በማድረግ የተገልጋዩን እርካታ የማሳደግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ቲጃኒ አክለዋል።

ከመሠረተ ልማት ግንባታዎች በተጨማሪ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የበርካታ አቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ያለውን ዕምቅ አቅም ለመጠቀም የተደረጉ ጥረቶች ውጤት አስመዝገበዋል

ሆሳዕና፤ ሰኔ 25/2018 (ኢዜአ) ፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ያለውን ዕምቅ አቅም በመጠቀም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማ...

Jul 4, 2026

የኦንላይን አገልግሎት መጀመሩ የሲቪልና የነዋሪነት አገልግሎትን ባለንበት ሆነን እንድናገኝ አስችሎናል 

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24/ 2018 (ኢዜአ):- ኤጀንሲው ያስጀመረው የኦንላይን አገልግሎት የሲቪልና የነዋሪነት አገልግሎትን ባሉበት ሆነው በቀላሉ እንዲያገኙ ማስቻ...

Jul 3, 2026

በኦሮሚያ ክልል የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የተጠናከረ የሰብል ጥበቃ ሥራ በቅንጅት እየተከናወነ ይገኛል

አዳማ ፤ ሰኔ 21/2018 (ኢዜአ):- በኦሮሚያ ክልል የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተቀናጀ የሰብል ጥበቃ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ...

Jun 29, 2026

በክልሉ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን ተደራሽ የማድረግ ተግባር ይጠናከራል-ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

ሚዛን አማን፣ ሰኔ 17/2018 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን ተደራሽ የማድረግ ተግ...

Jun 25, 2026