የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኃይል የማስተሳሰር ሚናዋን አጠናክራ ትቀጥላለች

Jul 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ሐምሌ 2 /2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኃይል የማስተሳሰር ሚናዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) ገለጹ።

​የ22ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር አስቸኳይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

ስብሰባውን አስመልክቶ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) ለመገናኛ ብዙኃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

​ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ለጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ሚናዋን እየተወጣች ነው።

በምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ማዕቀፍም ሀገሪቱ ቀጣናውን በኃይል የማስተሳሰር ተግባሯን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

​ይህ የኃይል ትስስር በቀጣናው አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖርና ትስስሩን ይበልጥ ለማሳለጥ አስቻይ መድረክ መሆኑንም አንስተዋል።

የኃይል አቅርቦትን በማሳለጥ የተረጋጋ የሕዝቦችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ ዋነኛው ግባችን ነው ብለዋል።

ለሁለት ቀናት እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ የምክር ቤት ስብሰባ በአባል ሀገራቱ መካከል በጋራ ለመሥራት የተደረጉ ስምምነቶች እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ውሎችን ጨምሮ በተለያዩ አሠራሮች ላይ ውይይት ተደርጎ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

​በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ገበያ ማዕከል የት ይሁን የሚለው ጉዳይ ሌላው ዋና የውይይት አጀንዳ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026